From Wikipedia, the free encyclopedia
ሶረን ኬርከጋርድ(5 ግንቦት, 1813 – 11 ህዳር, 1855) የነበረ ዴንማርካዊ ፈላስፋ እና ሥነ መለኮት ተማሪ ነበር። በብዙወች ዘንድ የመጀመሪያው የኅልውነት ፍልስፍና አፍላቂ ተደርጎ ይወሰዳል።
ኬርከጋር ብዙ ስለ እመንት፣ ኅልውነት፣ ስሜት የሚያትቱ የፍልስፍና መጻሕፍትን ጽፏል። ኬርከጋር ክርስትናን ፖለቲካዊ አቋም እንዲይዝ የሚተጉትን አጥብቆ ተቃውሟል፣ የግለሰብን ነጻነት በቡድን ነጻነት ለመወሰን የሚጥሩንም እንዲሁ ይቃወም ነበር፡፡ ስራው በብዙወች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈለት ሲሆን ሉድቂግ ዋይንሳታይን የተሰኘው የሃያኛው ክፍለ ዘመን ፈላስፋ "ካይከጋርድ" የአ19ኛው ክፍለ ዘመን ስር ነቀል አሳቢ እንደነበር ይገልጸዋል።
ኬርከጋርድ ኮፐንሃገን፣ ዴንማርክ ሲወለድ፣ በኮፐንሃገን ዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ተከታትሎ በ1841 ዲግሪውን አግኝቷል። ከሴት ጓደኛው ጋር ከተለያየ በኋላ ብዙ መጻህፍትን ሲደርስ፣ እኒህ መጽሃፎች በዘመኑ ያልተወደዱ በ20ኛውና በ21ኛው ክፍለ ዘመን ግን ተደናቂነትን ያገኙ ናቸው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.