ሸዋ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሽዋ በኢትዮጵያ ገጸ ምድር መሃል ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ሥፍራ ነው። ለብዙ መቶ ዓመታት በሉዐላዊነት በራሱ መሪዎች ሲተዳደር የኖረ የኢትዮጵያ አካል ሲሆን፣ ርዕሰ ከተማው እስከ ፲፰፻፹፱ ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ውስጥ በየጊዜው በተለያዩ ሥፍራዎች ሲፈራረቅ ቆይቶ ባለፉት መቶ በላይ ዓመታት ግን አዲስ አበባ ሆናለች። ደብረ ብርሃን፤ አንኮበር፤ አንጾኪያ፤ ልቼ እና እንጦጦ በተለያዩ ጊዜያት የሸዋ ርዕሰ ከተማዎች ነበሩ። የሸዋ ገጸ ምድር እምብርት ባሁኗ ኢትዮጵያ መሃል የሚገኙት ተራራዎች ናቸው። በአህመድ ግራኝ ወረራ ጊዜ የባሌ ክፍለ ሀገር ከተወሰደ በኋላ የሸዋ ድንበር የኢትዮጵያ የደቡብ-ምሥራቅ ድንበር ነበር። የግዛቱ ተራራማነት የተፈጥሮ መከላከያ በመሆን ከውጭ ወረራ ለመላ አገሪቱ ደጀን የነበረና በፍትህ የአስተዳደር ዝናውም ለሌላ የኢትዮጵያ ዜጋዎች መጠጊያና መሸሸጊያም ነበር። አንዳንዴም በወራሪ ሕዝቦች ምክንያት ከቀሪው የኢትዮጵያ ግዛቶች ተግንጥሎም አብዛኛው የሰሜን ሸዋ ግዛቶች፣ ማለትም ሰላሌ(ግራሪያ)፤መርሃቤቴ፤ ደራ፤ መንዝ፤ ተጉለት፤ ይፋት፤ ምንጃር እና ቡልጋ ሕዝብ ክርስቲያን አማራ እና ኦሮሞዎች ናቸው። ደቡብ እና ምሥራቅ ሸዋ ግን አብዛኛው የኦሮሞ ብሔር እና የእስላም ኃይማኖት ተከታዮች ናቸው። በሰሜን ሸዋ ብዙ ታሪካዊ አብያተ ክርሲያናት እና ገዳማት ይገኛሉ። ከነዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው፣ አቡነ ተክለ ኃይማኖት በሰላሌ ወረዳ የመሠረቱት ታዋቂው የደብረ ሊባኖስ ገዳም ይገኙበታል።
Selale Famous : Danny Mack
የሰላሌ ታዋቂ ሰው : Danny Mack