ቀይ ተኩላ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ቀይ ተኩላ ወይም ቀይ ቀበሮ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኝ አጥቢ እንስሳ ነው። በዘልማድ «ቀበሮ» ይባል እንጂ የተኩላ ዘር (የውሻ ወገን) ነው። የሚኖርበትም ስፍራ ከ3000 ሜትር ከፍታ በላይ ካሉ ቦታውች ብቻ ሲሆን፣ የሚገኘውም በብዛት ባሌ ተራራና ሰሜን ተራራ ነው። ከዚህ በተረፈ በጉና ተራራ፣ በመንዝ እና በወሎ አልፎ አልፎ ይገኛል። ቁጥሩም የተመናመነ ስለሆነ ሊጠፋ የደረሰ እንስሳ ተብሎ ይታወቃል።