የቢዛንታይን መንግሥት ወይም የሚሥራቃዊ ሮሜ መንግሥት387 እስከ 1445 ዓ.ም. ድረስ የቆየ መንግሥት ነበር። በ387 ዓ.ም. የሮሜ መንግሥት ለመጨረሻው ጊዜ ተለይቶ ምሥራቁ ግማሽ ልዩ መንግሥት ሆነ፤ ዋና ከተማው ቁስጥንጥንያ (ወይም «አዲሱ ሮሜ») ነበር። ከዚሁ ትንሽ በፊት ክርስትና በሮሜ መንግሥት ውስጥ የመንግሥት ሃይማኖት ሆነ። በ468 ዓ.ም. ሮሜ እራሱና የምዕራባዊ ሮሜ መንግሥትኦዶዋከር ወገን ወደቁ። በቁስጥንጥንያ ግን የሮሜ መንግሥት በረታ። እስከ 612 ዓ.ም. ድረስ ይፋዊ ቋንቋ ሮማይስጥ ሆኖ ቀረ፤ በዚያ አመት ግን የሕዝቡ መነጋገሪያ ግሪክኛ ይፋዊ ሆነ።

Thumb
ክሪስሞን
Thumb
የባይዛንታይን ግዛት መነሳት እና ውድቀት የታነመ ካርታ.

1196 እስከ 1252 ድረስ በመስቀል ጦርነት ምክንያት የቁስጥንጥንያ መንግሥት ለጊዜው ጠፋ። ከዚያ በኋላ ግዛቱ እየደከመ እስከ 1445 ዓ.ም. ድረስ ቀረ። በዚያው አመት የቱርክ ሰዎች ቁስጥንጥንያን ያዙ።

ቢዛንታይን የሚለው ስም ከቁስጥንጥንያ ጥንታዊ ስም «ቢዛንቲዮን» መጣ። ሆኖም ይህ ስም በታሪክ መጻሕፍት መጀመርያ በ1549 ታየ። በጊዜው የነበሩት ዜጋዎች ግን ራሳቸውን «ሮማዮይ» አገራቸውንም ሮሜ («ሩም») ይሉት ነበር።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.