ታኅሣሥ ፫
From Wikipedia, the free encyclopedia
ታኅሣሥ ፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፺፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፸፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፸፪ ቀናት ይቀራሉ።
ይቺ ዕለት በኢትዮጵያ ታሪክ ሁነኛ ስፍራ አላት። ታላቁ ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒልክና የጦሩ ፊታውራሪ፣ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲናግዴ ያረፉበት ዕለት ናት፡፡ ዕለቱ ተመሳሳይ ይሁን እንጂ ሁለቱ ያረፉት በተለያዩ ዓመታት ነው፡፡ ‹‹አባ ዳኘው›› የተባሉት፣ ዳግማዊ ምኒልክ ፳ኛው ምዕት ዓመት በባተ በስድስተኛው ዓመት ላይ በ፲፱፻፮ ዓ.ም. ሲያርፉ ‹‹አባ መላ›› የተሰኙት ፊታወራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ደግሞ በ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. አርፈዋል። ዓመታቱ ይለያዩ እንጂ ሁለቱም ያረፉት ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ነበር፡፡