ነጋሶ ጊዳዳ
From Wikipedia, the free encyclopedia
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቀድሞው የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
ዶ/ር ነጋሶ ከ1987 እስከ 1994 ዓም ጀምሮ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ዶ/ር ነጋሶ በወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ ባለመስማማታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ከለቀቁ በኋላም በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ በግል ዕጩነት የሕዝብ ድምጽ በማግኘት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆንም አገልግለዋል፡፡
ከመጀመሪያ ባለቤታቸው ደሲቱ ቀጀላ ሁለት ልጆችን ወልደዋል፡፡
በትምህርት እድል ከጀርመን ጎተህ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት የዶክትሬት ዲግሪአቸውን ያገኙት ዶ/ር ነጋሶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የታሪክ መምህር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
በጀርመን ሃገርም ረጊና አበልት የተባሉ ጀርመናዊት ነርስ እና አዋላጅ ጋር ትዳር በመመስረት አንድ ልጅ ወልደዋል፡፡