ዓባይ ማለት የናይል ወንዝ ታላቁ ገባር ወንዝ ሲሆን መነሻው ኢትዮጵያ ነው። አባይ 70 በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱን ወንዞች የውሃ ድርሽ ሲይዝ አጠቃላይ የውሃድርሻውም ቢሆን 50 በመቶ የሚጠጋ ነው። በኢትዮጵያ ከዓባይ ውጭ ያሉት ወንዞች ድምር ድርሻ 14 በመቶ ነው። ስለዚህ አባይ ለግብጽና ሱዳን ዋና የውሃ ምንጭ እንደሆነው ሁሉ ለኢትዮጵያም ዓባይ ወሳኝ ወንዟ ነው ማለት ይቻላል። በአሁኑ ወቅትም ኢትዮጵያ የአባይን ውሃ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ አባይ ለሚያቋርጣቸው አገራት እንዲደርስ የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገች ትገኛለች። በ2011 እ.ኤ.አ. የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ፦ ኢትዮጵያ ሌሎቹን የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች በማይጎዳ መልክ በአግባቡ የተቀየሰውን "ታላቁ የሕዳሴ ግድብ" ተብሎ የተሰየመውን 6000 ሜጋዋት የሚያመነጭ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግንባታ መጀመሯን በይፋ አስታውቃለች። ይህ ግድብ የሚገነባው በውጭ የሃብታም ሃገሮች የገንዘብ እርዳታ ሳይሆን በራሷ ሕዝቦች የገንዘብ መዋጮ መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚወች እየተገለፀ ነው።


Quick Facts ዓባይ ወንዝ (ናይል) ...
ዓባይ ወንዝ (ናይል)
ዓባይ ወንዝ በግብጽ
ዓባይ ወንዝ በግብጽ
መነሻ አፍሪቃ (ጥቁር አባይ ከኢትዮጵያ ይነሳል፣ ነጭ ዓባይ ደግሞ ከኃይቆች አካባቢዎች (መካከለኛ አፍሪካ) ይነሳል።)
መድረሻ መዲተራኒያን ባህር
ተፋሰስ ሀገራት ሱዳንደቡብ ሱዳንኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፓብሊክታንዛኒያኬንያኡጋንዳኢትዮጵያግብጽ
ርዝመት 6,650 km (4,132 mi)
ምንጭ ከፍታ 1,134 m (3,721 ft)
አማካይ ፍሳሽ መጠን 2,830 m³/s (99,956 ft³/s)
የተፋሰስ አካባቢ ስፋት 3,400,000 km² (1,312,740 mi²)
Close

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.