From Wikipedia, the free encyclopedia
አርተር ሾፐናውር (የካቲት ፲፮ ቀን ፲፯፻፹ – መስከረም ፲፪ ቀን ፲፰፻፶፫ ዓ.ም.) ጀርመናዊ ፈላስፋ ነበር።
በሾፐናውር እምነት የማናቸው ነገሮች ምንነት (ኢሴንስ) ፣ ሰዎችንም ጨምሮ፣ እውቀታቸው፣ ምክንያታዊነታቸው ወይምን መንፈሳቸው ሳይሆን ፈቃዳቸው ነው ይል ነበር። ፈቃድሲል ማናቸውንም ነገሮች፣ ከአለቶች ጀምሮ እስከ ሰው ልጅ ኅልው እንዲሆኑ የሚገፋቸውን ጉልበት ነው። ይህ ጉልበት ምንም ምክንያት የለውም፣ ኅልው ለመሆኑም ምክንያት የለውም፣ ስለሆነም የሰው ልጅ ስቃይ ከዚህ ምክንያት የለሽ እውር ጉልበት ይመነጫል ብሎ ሾፐናውር ያስተምር ነበር።
«የሰው ልጅ የሚፈልገውን ማድረግ ይችላል |
— ሾፐናውር |
ሾፐናውር ለዚህ ስቃይ ማስታገሻ ይሆናል ብሎ የዘየደው ፈውስ ሰወች የተሻለ ንቃተ ህሊና እንዲኖራቸው መምከር ነበር። የተሻለ ንቃተ ህሊና እንዴት ይገኛል ለሚለው የእርሱ መልስ የሰው ልጅ ፍላጎቱን ማሟላትን እንዲክድ፣ ጊዜ ሰውቶ እራሱን እንዲመረምርና ምን ቢሰራ ስቃዩን እንደሚያመልጥ በማሰብ ነው። ለስቃዩ ማምለጫ ከአዘዘው ውስጥ የኪነት ስራወችን መስራትና የተሰሩትን ማድነቅ፣ በተለይ ሙዚቃን ያጠቅሳል። ሙዚቃ፣ በሾፐናውር አስተሳሰብ፣ ለሰው ልጆች ኅልው መሆን (መኖር) አንዱ ምክንያት ነው።
ሾፐናውር ለሪቻርድ ዋግነር፣ ፍሬደሪክ ኒሺ፣ ሉድዊግ ዋይንስታይን፣ ሲግመንድ ፍሮይድ፣ ሊዮ ቶልስቶይ፣ ካርል ጀንግ እና ሌሎች ብዙ የምዕራቡ አለም የኪነትና ፈጠራ ሰወች ላይ ተፅዕኖ ያሳደረ ፈላስፋ ነበር።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.