አጋታርከስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
አጋታርከስ (Ἀγάθαρχος) ወይንም (Ἀγαθαρχίδης) ከክርስቶስ ልደት በፊት በሁለተኛው ክፍለ ዘመን (200-130 ዓ.ዓ.) ይኖር የነበር የግሪክ መልክዓ ምድር ተመራማሪ ነበር። ግሪክ ውስጥ ናይደስ እምትባል ቦታ የተወለደው አጋርታከስ በኋላ ወደ አሌክሳንድሪያ ሄዶ ግብጽ ውስጥ እንደኖረ ታሪኩ ይገልጻል። በግብጽ ህይወቱ ውስጥ መጀመሪያ አስተማሪነት ቢቀጠርም በኋላ ግን የሄራክሊደስ ጸሐፊ ለመሆን በቃ። ሄራክሊደስ እንግዲይ የቶሎሚ 6ኛ ወዳጅ የነበረና በኋላ ከአንጾክዮስ ጋር በተደረገው ጦርነት ወደ ሶሪያ አምባሳደር ሆኖ የተሾመ ነው። በሁለቱ ጦረኞች መካከል የሰላም ድርድር ሲደረግ ሄራክሊደስ ተካፋይ ስለነበር የአጋርታከስ የጠለቀ ዕውቀት በዚህ ጊዘ ከነበረው መረጃዎችን የመፈተን ዕድል ይመነጫል። ሆኖም በኋላ ቶሎሚ 8ኛ ሲነግስ ማናቸውም በቶሎሚ 6ኛ ጥቅም ያገኙ ጠቢባን እንዲሰደዱ እንጂ እንዳይጠቀሙ አዋጅ ወጣ። ስለሆነም አጋርታከስ እና ሌሎች ተማሪዎች ለብዙ ዘመን ከኖሩባት አሌክሳንድሪያ እንዲሰደዱ ሆነ።