የሷዴሽ ዝርዝር
From Wikipedia, the free encyclopedia
የሷዴሽ ዝርዝር በቋንቋ ጥናት የሚጠቀም የመሠረታዊ ቃላት ዝርዝር ነው። ስሙ ከቋንቋዎች ሊቅ ከሞሪስ ሷዴሽ የመጣ ነው። በዚሁ ዝርዝር ያላቸው ቃላት የልዩ ልዩ ልሣናት ዝምድና ለማነጻጸር ይጠቅማሉ።
አቶ ሷዴሽ ሁለት ዝርዝሮች ፈጠሩ፤ አንዱ 200 ቃላት ሲሆን ሌላው 100 ቃላት ብቻ አሉት። 100 ቃላት ባሉበት ዝርዝር ላይ 7 ተጨማሪ ቃላት (በ2 መቶ ቃላት ያልተገኙት breast, fingernail, full, horn, knee, moon, round) ስላሉ፣ በጠቅላላ 207 ቃሎች አሉ።