![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/e/e6/FTC_geometric.svg/langam-640px-FTC_geometric.svg.png&w=640&q=50)
የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ
From Wikipedia, the free encyclopedia
የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥ በሁለቱ ታላላቅ የካልኩለስ ክፍሎች፣ ማለትም በውድድር እና ጥርቅም (ጥረዛ) መካከል ያለውን ዝምድና የሚወስን የሒሳብ መሰረታዊ እርግጥ ነው።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/e/e6/FTC_geometric.svg/320px-FTC_geometric.svg.png)
መሰረታዊ እርግጡ በሁለት ይከፈላል።
የመጀመሪያው ክፍል፣ በአንድ አስረካቢ ላይ የሚካሄድ ውስን ያልሆነ መጠራቀምን በ ውድድር ሊመለስ እንደሚችል ያሳያል።
ሁለተኛው ክፍል የአንድን አስረካቢ ውስን ጥርቅም፣ በመደመር ሳይሆን፣ ኢውድድሩን በማስላት ለማግኘት ያስችላል።
የካልኩለስ መሰረታዊ እርግጥን መጀመሪያ ያገኘው የስኮትላንድ ተወላጁ ጄምስ ግሪጎሪ ሲሆን፣ በኋላም ኢሳቅ ባሮው፣ ተማሪው ኢሳቅ ኒውተን እና ጎትፍሪድ ሌብኒዝ እርጉጡን በማስፋፋትና በማብራራት ስማቸው ይጠራል።
መሰረታዊው እርጉጥ ሁለት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያው ክፍል፣ የኢውድድርን ውድድር በማግኘት ላይ ሲያተኩር፣ ሁለተኛው ክፍል፣ በኢውድድርና በጥረዛ ላይ ያተኩራል