ፐሽቶ
From Wikipedia, the free encyclopedia
From Wikipedia, the free encyclopedia
ፕሽቶ (پښتو) በአፍጋኒስታን በምዕራብ ፓኪስታን እንዲሁም በስሜን ሕንድ አገሮች በሚኖሩት በፓሽቱን ሕዝብ የሚናገር ቋንቋ ነው።
ከ1928 ዓ.ም. ጀምሮ ፐሽቶ ከዳሪ ፋርስኛ ጋራ ከአፍጋኒስታን ሁለት ይፋዊ መደበኛ ቋንቋ አንድ ነው። ከአፍጋኒስታን ኗሪዎች በ35 ከመቶ ወይም 22 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች እንደሚናገር ይገመታል።
ፐሽቶ ከአረብኛና ከቱርክኛ አያሌው ቃሎች ተበድሮዋል። በእስጅንደር ዘመን (ክ.በ. 330) ግሪኮች ይህን አገር ደረሱና አንዳንድ ሊቃውንት ከጥንታዊ ግሪክ ደግሞ የወረዱ ቃላት አሉ ብለው ይገመታሉ። በፓኪስታን ደግሞ ፐሽቶ የሚናገሩ 11-14 ከመቶ ወይም 13 ሚሊዮን ሰዎች ፐሽቶ እንደሚችሉ ይታመናል። በጠቅላላ 40-50 ሚሊዮን ያሕል ፐሽቶ ተናጋሪዎች አሉ።
ፕሽቶ በሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ውስጥ ሲካተት በዚያ ላይ በኢራናውያን ቋንቋዎች ዘርፍ ውስጥ ይደመራል።
ፐሽቶ እንደ አማርኛ ግሡ በዕረፍተ ነገሩ መጨረሻ የሚሳክበት ቋንቋ ነው። ቅጽል ከስሙ ይቀድማል። ስምና ቅጽል የተባይና የአንስታይ ጾታዎች፥ ነጠላና ብዙ ቁጥር፥ ሳቢና ተሳቢ አይነቶች አሉዋቸው። መስተጻምር የለም።
እስልምና ከተነሣ ጀምሮ ፐሽቶ የሚጻፍበት በአረብኛ ጽሕፈት አይነት ሆኗል. አንዳንድ ልዩ ድምጾች ስልላሉት ግን ተጨማሪ ምልክቶች ይኖራሉ። ፊደሉን በሙሉ ለመመልከት ወዲኅ Archived ጃንዩዌሪ 18, 2012 at the Wayback Machine ይሂዱ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.