ሃሙራቢ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሃሙራቢ (አካድኛ፤ ከአሞርኛ አሙራፒ) ከ1705 እስከ 1662 ዓክልበ. ድረስ ('ኡልትራ አጭር አቆጣጠር') የባቢሎን ንጉሥ ነበረ። አባቱ ሲን-ሙባሊት ማዕረጉን ከተወ በኋላ ወራሹ ሃሙራቢ የባቢሎንን መንግሥት ግዛት በሜስፖጦምያ በጦርነት አስፋፋ።[1]
ሃሙራቢ በተለይ የሃሙራቢ ሕገ ፍትሕ ስለሚባለው የ1704 ዓክልበ. ሕገ ፍትሕ ይታወቃል። ሕግጋቱ የተቀረጹ ቁመቱ 2.4 ሜትር በሆነ ድንጋይ ሲሆን በ1893 ዓ.ም. ለሥነ ቅርስ ተገኝቷል። ሃሙራቢ እንደ ሕግ-ሰጪ ንጉሥ ዝነኛ ስለሚሆን፣ ምስሉ በአሜሪካ መንግስት ቤቶች ዛሬው ሊታይ ይችላል።