የሉቃስ ወንጌል
የዘኬዎስ፡የስም፡ትርጉም / From Wikipedia, the free encyclopedia
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈው። ቅዱስ ሉቃስ ሙያው ጥንቃቄ የሚፈልግ ስለነበረ ወንጌልንም ሲፅፍ ትልቅ ጥንቃቄ እያደረገ ለምሳሌ ከቃሉ ምንጭ ከሆነች ከእመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ዘንድ ድረስ እየሄደ በማነጋገር እንደፃፈ ይነገርለታል። በተጨማሪም የሐዋርያት ሥራን የፃፈ ይሄው ቅዱስ ነው። ከቅዱስ ጳውሎስ ጋርም ብዙ ቦታዎች ላይ ተገኝቷል። እንዲሁም ጌታ ከሙታን ተለይቶ ምትን ድል አድርጎ በተነሣበት ቀን በፍኖተ ኢማሑስ (በኢማሑስ መንገድ) ጌታችን ከተገለጠላቸው ከሁለቱ ደቀመዛሙርት አንዱ ቅዱስ ሉቃስ እንደሆነ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያስተምራሉ።
Quick Facts ቅ.ሉቃስ ወንጌላዊው, የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ...
ቅ.ሉቃስ ወንጌላዊው | |
---|---|
የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል | |
የፀሐፊው ስም | ሉቃስ |
የተወለደበት ቀን | ጥቅምት ፳፪ በ፩ኛው ክፍለዘመን |
የተወለደበት ቦታ | አንፆኪያ (ሶርያ) |
ሥራው | ሐኪም፣ወንጌል ፀሐፊ፣ሰባኪ፣ሰዐሊ |
ያረፈበት ቀን | መጋቢት ወር ፹፬ ዓ.ም ግሪክ(ቦዬሺያ)ከተማ |
በዓለ ንግሥ | ጥቅምት ፳፪ |
ምልክቱ | |
የሚከበረው | በዓለም ክርስቲያን ሕዝብ |
የጻፈው ወንጌል | ፳፬ ምዕራፍ |
← የማርቆ.ወንጌ የዮሐን.ወንጌ → | |
Close
ወንጌላዊው ሉቃስ በላህም ይመሰላል ምክኒያቱም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት መወለዱን በእለተ ልደቱም የከብት እረኞች ከመላእክት ጋር መዘመራቸውን ከሌሎች ወንጌላውያን ሠፋ አድርጐ ስለሚተርክ ነው። (ሉቃ፡፪.፰-፲፰) ከዚህ ሌላ ላህም በብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት እንሰሳ ሲሆን ሉቃስም የክርስቶስን መስዋትነት በፍሪዳ ምሳሌ ጽፎአል። (ሉቃ፡፲፭.፳፪-፳፬) ላም የቀንድ ከብት ነው በዚሁም መሠረት ወንጌላዊው ሉቃስ ክርስቶስ ቀርነ መድኃኒት እንደሆነ ነብዩ ዘካርያስ የተናገረውን ትንቢት በመግለጽ ስለፃፈ የላህም ምልክት እንደተሰጠው መተርጉማን ሊቃውንት ይናገራሉ[1]።