From Wikipedia, the free encyclopedia
መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በትግራይ ክልል ርዕሰ ከተማ ከመቀሌ በአሥር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ዘመናዊ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ነው።
አየር ማረፊያው በዘመናዊ መልክ የተገነባ እና የተደራጀ ሲሆን ከባሕር ወለል በ ፪ሺ ፪መቶ ፶፯ ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። ባሁኑ ጊዜ አየር ማረፊያው አንድ ባለ ፫ሺ ፮፻ ሜትር ርዝመት በ፵፫ ሜትር ስፋት ያለው አስፋልት የለበሰ ማኮብኮቢያ ያለው ሲሆን እንደ ቦይንግ ፯መቶ ፶፯ አይነት አየር ዠበቦችን ማስተናገድ ይችላል። ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉት እንደ ጉምሩክ፣ ኢሚግሬሽን፣ የደህንነት ተቋማትና ኳራንቲን የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶችን ያሟላ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሕር-ዳርን እና መቀሌን ከካርቱም ጋር በማገናኘት ጥቅምት ፪ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ዓለም አቀፍ በረራ የጀመረ ሲሆን፣ የሁለቱን አገራት የንግድ፤ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ ለማሸጋገር የላቀ ሚና እንደሚኖረው ይገመታል። የበረራ መስመሩ በሳምንት ለአራት ቀናት የሚከናወን ሲሆን፣ ሰሜን ሱዳንን ከሰሜን የአገራችን ክፍል በቀጥታ የሚያገናኝ ነው። አየር መንገዱ ከሱዳን ለሚመጡ ጎብኝዎች የአባይ ወንዝን ምንጭ፤ የጢስ እሳት ፏፏቴን፤ በ፯ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገነባውን እና በአፍሪቃ የመጀመሪያው መስጊድ እንደሆነ የሚነገርለትን አል ነጃሺ መስጊድ እና ሌሎችንም የሰሜን ኢትዮጵያ መስህቦዎችን ለመጎብኘት እንደሚያመቻች ይታመናል።
ከዚህ በተጨማሪም መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በቅርቡ ያስገባውን፣ ፻፶ ቶን ማስተናገድ የሚችል ቀዝቃዛ መጋዘን በመጠቀም የአበባ፤ ፍራፍሬና አታክልት፤ ዓሣ እና የሥጋ ምርቶችን በቀጥታ ወደዓለም ገበያዎች ማጓጓዝ በቅርቡ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋ አድርጓል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.