From Wikipedia, the free encyclopedia
አንገልን (ጀርመንኛ፦ Angeln፤ ዳንኛ፦ Angel) በዛሬው ጀርመን አገር ውስጥ አነስተኛ ልሳነ ምድር ሲሆን በትልቁ ዩትላንድ ልሳነ ምድር ላይ ይገኛል። በስሜናዊ ክፍላገር በሽለስቭክ-ሖልሽታይን ውስጥ ተገኝቶ ለዴንማርክ ቀርቧል ማለት ነው።
በታሪክ ላይ ይህ መሬት ከ1856 ዓም አስቀድሞ ለረጅም ጊዜ የዴንማርክ አካል ነበር። ከ500 ዓም አካባቢ በፊት የአንግሊ ብሔር መናኸሪያ ነበር። ይህ ብሔር በ500 ዓም አካባቢ ከዚያ ተነሥተው ወደ ብሪታንያ ደሴት ፈለሱ፤ ስማቸውን ቋንቋቸውንም ለኢንግላንድ የሰጡ ሆነዋል። ቋንቋቸውም ጥንታዊ እንግሊዝኛ ሲሆን በዘመናት ላይ በተደራጀበት መጠን የዘመናዊ እንግሊዝኛ ምንጭ ሆነ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.