ማርኩስ ሳልዊዩስ ኦጦ ለአጭር ዘመን ለ፫ ወር ከጥር ወር 61 ዓም ጀምሮ የሮሜ መንግሥት ቄሣር ነበር። የአራቱ ቄሣሮች ዓመት ሁለተኛው ንጉሥ ነበረ።

Thumb
ኦጦ የሮሜ ቄሣር

ኦጦ በ24 ዓም በጣልያን ተወለደ። በሮሜ ግቢ፣ ነጉሥ ኔሮን እንደ ጎበዝ ወጣት ቆጠረው። ኔሮን ግን ሚስቱን ከቃመ በኋላ ኦጦን ወደ ሉሲታኒያ (ፖርቱጋል) እንደ አገረ ገዥ ላከው።

ጋሊያ ሉግዱኔንሲስ (ፈረንሳይ) እና የሂስፓኒያ ታራኮኔንሲስ (ስፔን) ክፍላገራት አገረ ገዦች በአመጽ ሲነሡ ኦጦም ከጸረ-ኔሮን ወገን ጋራ ተባበረ። ኔሮን ራሱን ከገደለ በኋላ የሂስፓኒያ አገረ ገዥ ጋልባ ቄሣር ሆነ።

Thumb
የኦጦ መሀለቅ

በጥር ወር 61 ዓም የጌርማኒያ ሥራዊት በጋልባ ላይ አመጹበትና የጌርማኒያ አገረ ገዥ ዊቴሊዩስ ንጉሥ እንዲሆን አዋጁ። ጋልባ በሮሜ ቆይቶ አልጋ ወራሹ ሉኪዩስ ካልፒኒዩስ ፒሶ እንዲሆን ሰየመው። በዚህ ኦጦ በተለይ ተናደደ፣ አልጋ ወራሽነቱን ለራሱ መኝቶ ነበርና። የሮሜ ሥራዊት ደግሞ ኦጦን ደገፈውና በጋልባ ላይ አመጹ። ጋልባ በድካምነቱ በቃሬዛ ተሸክሞ ሲቀርብላቸው ገደሉትና ያንጊዜ ኦጦ ለአጭር ወራት በፈንታው የሮሜ ቄሣር ሆነ። መልኩ ለኔሮን ተመሳሳይነት ስለነበረው በሮሜ ዜጎች መኃል እንደ አዲሱ ኔሮን ተወደደ። የኔሮንም ሰዶማዊ «ባል» ስፖሩስ ለራሱ «አገባ»።

ከዚያ ኦጦ የጋልባን ሰነዶች አንብቦ የዊቴሊዩስ ሥራዊት ከጌርማኒያ ቶሎ እንደሚደርስ ተረዳ። የዊቴሊዩስ ወገን ወደ ጣልያን ገብቶ አሸንፎም ኦጦ ብሔራዊ ጦርነት እንዳይስፋፋ እንደ ኔሮን ራሱን እንደ ገደለ ይባላል። ስለዚህ በፈንታው ዊቴሊዩስ በሚያዝያ የሮሜ ቄሣር ሆነ።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.