1991 አመተ ምኅረት

  • ጥቅምት ፳ - «ሃሪኬን ሚች» የተባለው ታላቅ አውሎ ነፋስ ባስከተለው የጭቃ ጎርፍ ኒካራጓ ላይ በጥቂቱ ሁለት ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ።
  • ኅዳር ፬ - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን በአመንዝረኛነት ፖላ ጆንስ በተባለች ሴት ተከሰው ለአራት ዓመታት ከተከራከሩ በኋላ ጥፋተኛነታቸውን ሳያምኑ ስምንት መቶ ኃምሳ ሺህ [[የአሜሪካ ዶላር] በመክፈል ክርክሩን አዘጉ።
  • ኅዳር ፲ - በአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የሕግ ሸንጎ በሞኒካ ሌዊንስኪ የአመንዝራ ኃጢአት በፈጸሙት በፕሬዚደንት ክሊንተን ላይ የክሱ ዝርዝር እና ምስክሮች መሰማት ጀመረ።
  • ኅዳር ፳፯ - በቬኔዙዌላ አገር ወታደራዊው መኮንን ሁጎ ሻቬዝ ፍሪያስ በፕሬዚደንትነት ተመረጠ።
  • የካቲት ፳፩ - የኢትዮጵያ ሠራዊት በኤርትራ ወራሪ ሠራዊት ላይ የባድመ ድል ተቀዳጀ።
  • ሚያዝያ ፩ - የኒጄር ፕሬዚደንት ኢብራሂም ባሬ ማይናሳራ በአገሪቱ በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተገደሉ።
  • ሐምሌ ፱ - የሟቹ የፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ልጅ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ጁንየር ከሚስቱ እና ከሚስቱ እህት ጋር በበረራ ላይ እንዳሉ በአውሮፕላን አደጋ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ በመስመጥ ሕይወታቸውን አጡ።
  • ሐምሌ ፲፮ - የሞሮኮው ንጉሥ ዳግማዊ ሀሰን ሲሞቱ ንጉሥ ሞሐመድ አራተኛ ተብለው የንጉሥነት ዘውድ ጭነው ነገሡ።
  • ነሐሴ ፭ - በአውሮፓ እና በእስያ አኅጉራት ያሉት በአውሮፓውያን አቆጣጠር የምዕተ ዓመቱን የመጨረሻ ድፍን የፀሐይ ግርዶሽ ተመልክተዋል።
Quick Facts
ክፍለ ዘመናት፦ 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት
አሥርታት፦ 1960ዎቹ  1970ዎቹ  1980ዎቹ  - 1990ዎቹ -  2000ዎቹ  2010ሮቹ  2020ዎቹ

ዓመታት፦ 1988 1989 1990 - 1991 - 1992 1993 1994
Close

ዕለተ ሞት

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.