ሉጋላንዳ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ሉጋላንዳ
Remove ads

ሉጋላንዳ (ሉጋል-አንዳ) ከ2109 እስከ 2102 ዓክልበ. ግድም የላጋሽ ከተማ ገዢ (ኤንሲ) በሱመር ነበር። ኤነታርዚን ተከተለው፣ እስከ 2107 ዓክልበ ድረስ ለአዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ መንግሥት ተገዥ እንደ ነበር ይመስላል። የሉጋላንዳ አባት የላጋሽ ቄሳውንት አለቃ ሆኖ ልጁን ሉጋላንዳን ለኤንሲ-ነቱን እንደሾመው ይመስላል።

Thumb
የሉጋላንዳ ማሕተሞች የአውሬዎቹን መረንነት ያከብራሉ።

እንደ ቀዳሚው ኤነታርዚ፥ ሉጋላንዳ ከቄሳውንት ወገን የሆነ ከባድ ገዢ ነበር። እርሱና ንግሥቱ ባራናምታራ በላጋሽ ካለው መሬት አብዛኛውን የግል ርስታቸውን አደረጉ። በቅንጦት እየተቀመጡ ሕዝባቸውንም በቀረጥ ብዛት እያሸከሙ እያደሃዩም በመዝገቦቹ ዘንድ እንደ ጭቆና ዘመን ይታወሳል። ባራናምታራ እራስዋ ከፍተኛ አምባገነን ስትሆን ከሉጋል-አኔ-ሙንዱ ንግሥት ጋር ንግድ እንዳካሄደች ታውቅል።

Thumb
የንግሥት ባራናምታራ ማሕተም።

ከዚህ ዘመን ብዙ መቶ ሰነዶች ከነዓመቶች ቁጥር (እስከ «ሉጋላንዳ 7ኛው ዘመነ መንግሥት» ድረስ) ይታወቃሉ።[1] ስለዚህ ሉጋላንዳ ከ7 ዓመታት በላይ እንደ ነገሠ አይመስልም።

በመጨረሻ የላጋሽ ሕዝብ ተቸግረው በአብዮት ተነሡና መንፈቅለ መንግሥት ወጣ። የላጋሽ አዲስ ንጉሥ ኡሩካጊና ብዙ ማሻሻያና ለውጦች አገባ፣ ባወጣውም ሕገ መንግሥት የደሆቹን መብቶች አስጠበቀ።


ቀዳሚው
ኤነታርዚ
ላጋሽ ኤንሲ
2109-2102 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኡሩካጊና
Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads