ሉጋል-አኔ-ሙንዱ

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ሉጋል-አኔ-ሙንዱ (22ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ገደማ) በሱመርአዳብ ከተማ-አገር ንጉሥ (ሉጋል) ነበረ። በሱመራዊ ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ፣ የዑር ንጉሥ መስኪአጝ-ናና ከተሸነፈ በኋላ፣ የሱመር ላዕላይነት ወደ አዳብ ተዛውሮ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ ለ90 አመታት እንደ ነገሠ ይላል። በተለይ የሚታወቀው በኋላ ዘመን በተቀረጸው ጽላት ቅጂ ነው።

የርሱ መንግሥት በመሞቱ ተከፋፈለ። በነገሥታት ዝርዝሩ መሰረት፣ ላዕላይነቱ («ቅዱስ ከተማው» ኒፑር የሰጠው) መጀመርያ ወደ ማሪ ከተማ ሥርወ መንግሥት ተዛወረ። ነገር ግን ከዚሁ ሥርወ መንግሥት ነገሥታት መካከል፣ መጨረሻው ብቻ እርሱም ሻሩም-ኢተር ላዕላይነቱን ከሉጋል-አኔ-ሙንዱ ቀጥሎ እንደ ያዘው የሚል ሀሣብ ቀርቧል።[1] በአዳብ መንግሥት መከፋፈል፣ ሌሎች ትልልቅ ከተሞች ደግሞ አንድላይ ነጻነታቸውን ሁለተኛ አገኙ፣ ለምሳሌ ላጋሽ (ንጉሥ ሉጋላንዳ)፣ አክሻክ (ከትንሽ በኋላ ላዕላይነቱን ከማሪ የያዘው፣ ምናልባት በፑዙር-ኒራሕ ሥር) እና ኡማ (ንጉሣቸው ሉጋል-ዛገ-ሲ በመጨረሻ አገሮቹን ሁሉ በፈንታው ያሸነፈው)።

Remove ads

«የሉጋል-አኔ-ሙንዱ ጽሑፍ»

«የሉጋል-አኔ-ሙንዱ ጽሑፍ» በሁለት ቅጂዎች በፍርስራሽ ሲታወቅ፣ እነርሱ በባቢሎን ነገሥታት አቢ-ኤሹህ እና አሚ-ሳዱቃ ዘመናት (ቢያንስ ከ500 አመታት በኋላ) ተቀረጹ። በዚህ ጽላት መሠረት፣ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ አገሮቹን ሁሉ በማሸነፉ «የአራቱ ሩቦች ንጉሥ» ሆነ። ይህ ግዛቱ ከዛግሮስ ተራሮች እስከ ሜዲቴራኔያን ባሕር ድረስ ይዘረጋ ነበር። የግዛቱ ክፍላገሮች ኤላምማርሃሺጉቲዩምሱባርቱ፣ «ደብረ አርዘ ሊባኖስ»፣ ማርቱሱትዩም[2] እና «ደብረ ኤ-አና» (ኡሩክ?) ነበሩ። «የአገሮቹ ሁሉ አሕዛብ በሰላም፣ በሜዳ ላይ እንደ ሆነ፣ አኖራቸው» ይላል።

በተጨማሪ ክፍላገሮቹ ሁሉ በአመጽ እንደ ተነሡበት ይላል። ከ13 አመጸኞች አለቆች ጋር ተዋጋ፤ ዋናውም የማርሃሺ አለቃ፣ ሚጊር-ኤንሊል ነበር። የሁላቸውም ስሞች እንደ «ሴማዊ» ስሞች ይቆጠራሉ።[3]

1926 ዓ.ም. ሊቁ ሃንስ ጉስታቭ ጊውተርቦክ አስተርጎመው፤ ነገር ግን ሀሣዊ ታሪክ ይሆናል በማለት ፈጥኖ ሻረው። ዳሩ ግን፣ ከዚያ አንዳንድ ሌሎች የሱመር ታሪክ ሊቃውንት ለምሳሌ ሳሙኤል ክሬመር ምናልባት ከዕውነተኛ የሉጋል-አኔ-ሙንዱ ጽሑፍ ተቀዳ በመገመት ባዮች ናቸው።[4]

Remove ads

ነጥቦች

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads