መስከረም ፳፯
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፳፯ኛው ዕለት እና የመፀው ወቅት ፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነሉቃስ ፫፻፴፱ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ማቴዎስ እና ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፰ ዕለታት ይቀራሉ።
ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- ፲፱፻፲፪ ዓ/ም - የሆላንድን ብሔራዊ ዓርማ ያዘለው ‘ኬ. ኤል. ኤም’ (KLM) የተባለው እና ከምሥረታው ጀምሮ እስካሁን ስሙንም ሆነ ዓርማውን ሳይቀይር በመቆየት አንደኝነትን ያስመዘገበው ዓየር መንገድ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፳፩ ዓ/ም - ልዑል ራስ ተፈሪ መኮንን በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ እጅ ዘውድ ጭነው ንጉሥ ተፈሪ ተባሉ። [1]
<<ለእኔ ረዳት እንድትሆን እነሆ ለክብርህ ዘውድ ሰጠሁህ። ወደፊትም ለንጉሠ ነገሥቱ ዘውድ ወራሽ ለመሆን ያብቃህ።>>[2] ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ፣ መስከረም ፳፯ ቀን ፲፱፻፳፩ ዓ/ም
- ፲፱፻፳፮ ዓ/ም - አምሥት ነባር የፈረንሳይ አየር መንገዶችን በማዋሐድ የአሁኑ ‘ኤየር ፍራንስ’ (Air France) ተመሠረተ።
- ፲፱፻፵፪ ዓ/ም - የቀድሞው የምሥራቅ ጀርመን ሪፑብሊክ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - ናይጄሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሆነች።
- ፲፱፻፷፬ ዓ/ም -ኦማንየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓባል ሆነች።
Remove ads
- ፲፱፻፵፭ ዓ/ም - አገራቸውን ሩሲያን በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር እና አሁን በፕሬዝዳንት ማዕርግ የሚያገለግሉት ቭላዲሚር ፑቲን በዚህ ዕለት ተወለዱ።
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads