ሳና

From Wikipedia, the free encyclopedia

ሳና
Remove ads

ሳና (ዓረብኛ፦ صنعاء /ሰንአ/) የየመን ዋና ከተማ ነው።

Thumb
የሳና አይነተኛ ፎቅ

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር ከ1996 ቆጠራ 1,747,627 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 15°24′ ሰሜን ኬክሮስ እና 44°14′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

Thumb
1000 አመት እድሜ ያለው ባብ አል-የመን (የየመን በር) በከተማው መሃል

ሳና በጣም ጥንታዊ ከተማ ሆኖ ቢያንስ ከ6ኛ ክፍለ-ዘመን ከክርስቶስ በፊት ተመሠረተ። በ500 ዓ.ም. ገዳማ የሂምያሪት መንግሥት ዋና ከተማ እንደ ነበረች ይታመናል። እንዲሁም ከ512 የአክሱም ንጉሥ ካሌብ እንደራሴ መቀመጫ ሆነ። እንደገና ከ562 ዓ.ም. ጀምሮ የፋርስ እንደራሴ መቀመጫ ሆነ። ከዚያ እስልምና ከተነሣ በኋላ ከተማው በአረብም ሆነ በቱርክ ሥልጣን ሁልጊዜ የአውራጃ መቀመጫ ሆኖ ቀረ። ለ1,500 አመት ገዳማ እስከ ዛሬ እንደ ዋና ከተማ ቆይቷል ማለት ነው።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads