ሲን-ኢቂሻም

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ሲን-ኢቂሻም ከ1751 እስከ 1746 ዓክልበ. ድረስ (ኡልትራ አጭር) የላርሳ ንጉሥ ነበረ። ከአባቱ ሲን-ኤሪባም ዘመን ቀጥሎ ለ5 አመት ነገሠ።[1] [2] [3]

5 የአመት ስሞቹ በሙሉ ይታወቃሉ። በነዚህ መሠረት፣ በ2ኛ አመት (1750) ፒናራቲምንና ናዛሩምን እንደ ያዘ፣ በ5ኛውም አመት (1747) የኢሲንን ንጉስ ዛቢያን እንዳሸነፈው ይዘገባል። ዛቢያም ከ1749 እስከ 1747 ድረስ በኢሲን መግዝቱን ይወስናል።

ሲን-ኢቂሻም ኢሲንን ብቻ ሳይሆን ካዛሉንም ኤላምንና ባቢሎንን በ1747 እንዳሽነፋቸው ይዘገባል። በ1746 ግን ሲሊ-አዳድ ለትንሽ ጊዜ የላርሳ ንጉሥ ሆነ።

ቀዳሚው
ሲን-ኤሪባም
ላርሳ ንጉሥ
1751-1746 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሲሊ-አዳድ
Remove ads

ነጥቦች

የውጭ መያያዣ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads