ስታምፎርድ ብሪጅ (የእግር ኳስ ሜዳ)

From Wikipedia, the free encyclopedia

ስታምፎርድ ብሪጅ (የእግር ኳስ ሜዳ)
Remove ads

ስታምፎርድ ብሪጅፉልሃም ለንደን የሚገኝ የቼልሲ እግር ኳስ ቡድን የእግር ኳስ ሜዳ ነው። የእግር ኳስ ሜዳው የሚገኘው በሙር ፓርክ ኢስቴት (በሌላ አጠራር በዋልሃም ግሪን) ወይም በተለምዶ ዘ ብሪጅ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ነው። ይህ የእግር ኳስ ሜዳ 41,798 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፣ ከፕሪሚየር ሊጉ ስምንተኛ ትልቅ የእግር ኳስ ሜዳ ያደርገዋል።

Thumb
ስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም

የተከፈተው እ.ኤ.አ በ1877 ሲሆን እስከ 1905 ድረስ የለንደን አትሌቲክስ ክለብ ይጠቀምበት ነበር። ሜዳው ብዙ ለውጦችን አካሂዷል። በቅርቡ ደግሞ (እ.ኤ.አ 1990ዎቹ) ወደ ዘመናዊና ለሁሉም ተመልካቾች መቀመጫ ያለው ሆኖ ተሠርቷል።

ስታምፎርድ ብሪጅ የተለያዩ የእንግሊዝ ዓለም አቀፋዊ ጨዋታዎችን ፣ የኤፍ ኤ ካፕ ፍጻሜዎችን ፣ የኤፍ ኤ ካፕ ግማሽ ፍጻሜዎችን እና የቻሪቲ ፊልድ ጨዋታዎችን አስተናግዷል። ለተለያዩ ስፖርቶችም እንደ ክሪኬትራግቢ ዩኒየንስፒድዌይግሬይሃውንድ ሬሲንግቤዝቦል እና የአሜሪካን ፉትቦል ጨዋታዎችን ለማስተናገድ ጥቅም ላይ ውሏል። የስታዲየሙ ትልቁ ኦፊሲዬላዊ የታዳሚዎች ቁጥር 82,905 ሲሆን ፤ ይህ የሆነው ቼልሲ ከአርሰናል እ.ኤ.አ በኦክቶበር 12 1935 ባካሄዱት የሊግ ጨዋታ ነበር።

Remove ads

ታሪክ

የቀድሞ ታሪክ

Thumb
የስታምፎርድ ብሪጅ ሜዳ የላይኛው ዕይታ - እ.ኤ.አ 1909

ስታምፎርድ ብሪጅ ፣ ሳምፎርድስብሪጅ (ጥንታዊ እንግሊዝኛ፦ Samfordesbrigge) ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ሳንዲ ፎርድ ላይ ያለው ድልድይ ማለት ነው። የዐሥራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን ካርታዎች በአሁኑ ጊዜ በምስራቅ ዳፍ ጀርባ በሚገኘው የባቡር መስመር የሚፈስሰውን የስታንፎርድ ጅረት (እንግሊዝኛ፦ Stanford Creek) የቴምስ ወንዝ ገባር እንደሆነ አድርገው ያሳዩ ነበር። የገባሩ ወንዝ የላይኛው ጫፍ ቢሊንግስዌል ቦይ (Billingswell Ditch)፣ ፑልስ ጅረት (Pools Creek) እና ካውንተርስ ጅረት (Counters Creek) በመባል ይጠራ ነበር። በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ፤ ይህ ጅረት ቢሊንግዌል ዲች የሚባል ስም ነበረው። ቃሉ የመጣውም የቢሊንግ ምንጭ ወይም ጅረት ከሚለው ነው። ይህም በፉልሃም እና በኬንሲንግተን ደብሮች መሀል ወሰን ፈጥሮ ነበር። በዐሥራ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን፤ አሁን በሚጠራበት ስሙ የካውንተር ጅረት በመባል መጠራት ጀመረ።

ጅረቱ ሁለት ድልድዮች ነበሩት ፤ እነርሱም በፉልሃም መንገድ ላይ የሚገኘው የስታምፎርድ ድልድይ (ስታምፎርድ ብሪጅ) (Stamford Bridge) እና በኪንግስ መንገድ ላይ የሚገኘውና በአሁኑ አጠራሩ ስታንሊ ድልድይ (ስታንሊ ብሪጅ) የተባለው የስታንብሪጅ ድልድይ ናቸው። በአሁኑ ጊዜ የሚገኘው የስታምፎርድ ድልድይ እ.ኤ.አ በ1860 ከጡብ የተሠራ ሲሆን ከዚያ ጊዜ በኋላ በከፊል ጥገና ተደርጎለታል።

Thumb
አዲሱ የስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በኦገስት 1905 እ.ኤ.አ

ስታምፎርድ ብሪጅ ፤ የለንደን አትሌቲክስ ክለብ ስታዲየም ሆኖ እ.ኤ.አ በ1877 ተከፈተ። በዚያ ሜዳ ላይ ታላላቅ የእግር ኳስ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት የፈለጉ ገስ እና ጆሴፍ ሚየርስ የተባሉ ወንድማማቾች ኮንትራቱን እስካገኙበት ጊዜ ድረስ ለለንደን አትሌቲክስ ክለብ እስከ እ.ኤ.አ 1904 ድረስ አገልግሏል።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads