ቡልጋ

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ቡልጋአማራ ክልልሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኝ ወረዳ ሲሆን አቀማመጡ በአብዛኛው ከቆላ እስከ ወይና ደጋ ነው። የወረዳው አስተዳደር ፣ የሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ ሲባል ሀገረ ማርያም (ሾላ ገበያ ) የሚባለው የገጠር ከተማ ላይ ይገኛል።

በወረዳው ውስጥ የዳግማዊ ምኒልክ ምሽግና የመሳሪያ ግምጃ ቤት የነበረችው ኮረማሽ የምትገኝበት ወረዳ ሲሆን እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች እንደሚያውቁት ቡልጋ የብዙ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን እና ቅዱሳት የትውልድ አገርም ነች።

፲፱፻፺፱ ዓ/ም የሕዝብ ቆጠራ ውጤት እንደሚያመለክተው በወረዳው ውስጥ ፶፭ ሺህ ፪፻፩ ሰዎች ሲኖሩ የወንዶች ብዛት ፳፰ ሺህ ፫፻፸፭ እና ሴቶች ደግሞ ፳፮ ሺህ ፰፻፳፮ እንደሆኑ ይጠቁማል። ከነኚህ ቡልጎች ፶፫ ሺህ ፲፭ቱ ሰዎች የገጠር ነዋሪዎችና በግብርና የተሠማሩ አርሶ አደሮች እንደሆኑ ያረጋግጣል።[1]

Remove ads

ታሪክ

የታወቁ የቡልጋ ተወላጆች

  • ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ- ቅዱስጌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዕርዳታ ብዙ ሺህ ነፍሳትን ከሲዖል ያወጣች
  • አክሊሉ ሀብተ-ወልድ ( ፀሐፌ ትዕዛዝ ) ዲፕሎማት፣ አምባሳዶር፣ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የውጭ ጉዳይ፤ የጽሕፈት ሚኒስቴር፣ ጠቅላይ ሚኒስቴር
  • ተስፋ ገብረ ሥላሴ የፊደል ገበታን የሰሩ የዕውቅት አባት
  • ሎሬት ዶ/ር መላኩ ወረደ የAlternative Nobel Prize ተሸላሚ ሳይንቲስት
  • ጌታቸው በቀለ - ቅንበቢት የኢ.ን.ነ.መ. ሚኒስቴር፣ አምባሳዶር
  • [አርበኛ እና የባህል ሐኪም ማሞ ኃይሌ ዘብሔረ ቡልጋ ከሰም]
Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads