ኒዌ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ኒዌ
Remove ads

ኒዌ Niue በፓሲፊክ ውቅያኖስ የሚገኝ የኒው ዚላንድ ራስ-ገዥ ደሴት አገር ነው።

Quick facts ኒዌNiuēNiue ...

ደሴቱ መጀመርያ በኢንግላንድ ተጓዥ ጄምስ ኩክ1766 ዓም ተዘገበ። የክርስትና ሰባኪዎች ከ1838 ዓም ጀምሮ ደርሰው የኗሪዎቹ ብዛት የክርስትና ምዕመናን ሆነዋል። መጀመርያው ክርስቲያን ንጉሥ ቱዊ-ቶጋ ከ1867-1879 ነገሠ።

1881 ዓም የፈረንሳይ ቅኝ አገር እንዳይሆኑ ፈርተው በራሳቸው ልመና በዩናይትድ ኪንግደም ጥብቅና ሥር ገቡ፤ በ1893 ዓም ጥብቅናው ወደ ኒው ዚላንድ ተዛውሮ እስካሁን ድረስ ከኒው ዚላንድ ጋር ተባባሪነት አላቸው። ሕዝቡ ግን ምንጊዜም በተግባር ራስ ገዥ ሆነዋል።

ይፋዊ ቋንቋዎች እንግሊዝኛ እና ኒዌኛ ናቸው፤ ብዙዎቹም ኒዌኛ ይናገራሉ። ደሴቱም 14 መንደሮች አሉበት።

ትንሽ ኮኮነትማርፓፓያ፣ ወዘተ. ለአለም ገበያ ይመረታሉ። የእጅ ሥራዎች፣ ፣ የቴምብር፣ የእግር-ኳስ መፈብረክ፣ የቱሪስም ኢንዱስትሪዎች አሉ።

ዛሬ የኒዌ ኗሪዎች ሁሉ (1600 ያህል) ኢንተርኔት አላቸው። ራግቢ ከሁሉ የሚወድ እስፖርት ጨዋታ ነው። ባህላዊ ጭፈራዎች አሉ።

ብዙዎቹም በግብርና ሥራ ሲገኙ፣ ለራሳቸው አበሳሰል ካሳቫጎደሬዳቦ ፍሬሙዝ፣ ፓፓያ፣ ኮኮነት፣ ኮቴሃሬ ይመርታሉ። በዋናነት የሚበላው አሣ ነው፣ እንዲሁም ሠርጣንአሳማ ይበላሉ። በምግብ አሠራሮቹ መካከል፣ «ናኔ ፒያ» ከፖሊኔዥያ አሮውሩትና ከኮኮነት የሚሠራ አጥሚት ነው።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads