ኒው ዚላንድ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ኒው ዚላንድ
Remove ads

ኒው ዚላንድ በደቡብ ምዕራብ ፓሲፊክ ውቅያኖስ የምትገኝ የደሴት ሀገር ናት።

Quick Facts ኒው ዚላንድNew ZealandAotearoa ...
Remove ads

ቋንቋዎች

በኒው ዚላንድ በዋንነት የሚነገረው መደበኛ ቋንቋ እንግሊዝኛ ነው። ማዖሪኛ በተለይ በማዖሪ ብሔር ይነገራል፣ በ1979 ዓ.ም. ደግሞ ይፋዊ ቋንቋ ሆነ። ከ1998 ዓ.ም. ጀምሮ የአገሩ ሦስተኛው ይፋዊ ቋንቋ የኒው ዚላንድ እጅ ምልክት ቋንቋ ሆኗል።

ባህል

ከኒው ዚላንድ ሕዝቦች መካከል የማዖሪ ብሔር ከሁሉ ይልቅ ለረጅም ዘመን በደሴቶቹ ላይ ኑረዋል። ማዖሪዎች «ሃካ» ስለ ተባለው ባህላዊ የውግያ ጭፈራ ታውቀዋል። በኒው ዚላንድ ባሕል ደግሞ የአገሩ ስፖርት (በተለይ የራግቢ) ቡድኖች ጨዋታ ሳይጀምሩ ሁልጊዜ «ሃካ» ይጨፍራሉ።

አንዳንዴ በቀልድ የኒው ዚላንድ ባህል ዓምዶች «ሦስቱ Rዎች» ይባላሉ - እነሱም «Rugby Racing እና beeR» (ራግቢ፥ እሽቅድድምና ቢራ) ናቸው። እንዲያውም የፈረስ እሽቅድድም አሁን እንደ ቀድሞ ደረጃ የተወደደ አልቆየም፣ ራግቢ እና ቢራ ግን ዛሬውንም በኒው ዚላንድ ሕዝብ በኩል በጣም የሚወደዱ ሆነው ቀርተዋል።

የኒው ዚላንድ ሰዎች አንዳንዴ በመጫወት ሲሆን በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ዘንድ «ኪዊዎች» ይባላሉ። «ኪዊዎች» በተለመደው (በጅምላ አመለካከት) ተጨባጭ ያልሆነ ኀልዮ ወይም አሣብ ሳይሆን ተግባራዊ ጉብዝና እና ሙያ ይመርጣሉ። ኒው ዚላንድ ለረጅም ዘመን በክፍሎች ያልተመደበ ሕብረተሰብ ይቆጠር ነበር - ከሃብታሞችና ደሃዎች ኒው ዚላንድ ኗሪዎች መካከል የነበረው ልዩነት ያንስ ነበር ማለት ነው። በቅርቡ ባለፉት አሥርታት ግን ይሄው ሁናቴ ተቀይሯል።

ብዙ የዚው ዚላንድ ኗሪዎች አድገው ወደ ውጭ አገሮች ይጎበኛሉ፣ ብዙዎቹም የባህላዊ ልውውጥ ፕሮግራሞች ይጠቅማሉ፣ ስለዚህ በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ፣ በተለይም በአውስትራሊያብሪታንያአውሮፓእስያ ይጓዛሉ።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads