አልጄሪያ

From Wikipedia, the free encyclopedia

አልጄሪያ
Remove ads

አልጄሪያ (አረብኛ፦ الجزائر‎ አል ጃዝኤር; በርበርኛ፦ ድዜየር) በይፋ የአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክሰሜን አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። ከቆሳ ስፋት አኳያ በሜዲቴራንያን ባህር ዙሪያ ትልቋ ስትሆን፣ ከአፍሪካ ደግሞ ከሱዳን በኋላ ሁለተኛ ናት።

Quick Facts الجمهورية الجزائرية الديمقراطية الشعبيةየአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ...

አልጄሪያ ከሰሜን ምሥራቅ በቱኒዚያ፣ ከምሥራቅ በሊቢያ፣ ከምዕራብ በሞሮኮ፣ ከደቡብ ምዕራብ በምዕራባዊ ሣህራሞሪታኒያማሊ፣ ከደቡብ ምሥራቅ በኒጄር፣ ከሰሜን በሜዲቴራንያን ባህር ትዋሰናለች። ዋና ከተማዋ አልጂርዝ ሲሆን የ፳፻፫ ዓ.ም. ሕዝብ ብዛቷ ወደ 35.7 ሚሊዮን ይገመታል።

አልጄሪያ የተባበሩት መንግሥታትየአፍሪካ ሕብረትኦፔክ እና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አባል ሀገር ናት።

Remove ads

ስም

የሀገሯ ስም የመጣው ከአልጂርዝ ከተማ ሲሆን በድሮ ጊዜ ከዛሬዎቹ ምዕራብ ቱኒዚያና ምሥራቅ ሞርኮ አብራ ኑሚዲያ ትባል ነበር።

ታሪክ

Thumb
ማሲኒሳ፣ የኑሚዲያ ታዋቂ ንጉሥ

በጥንት ጊዜ አልጄሪያ የኑሚዲያ መንግሥት ትባል የነበረ ሲሆን ነዋሪዎቿ ደግሞ ኑሚዲያውያን ይባሉ ነበር። የኑሚዲያ መንግሥት ከካርታጎሮማጥንታዊ ግሪክ ጋር ግንኙነት ነበራት። አካባቢው ለምለም እንደነበረ ሲነገር ኑሚዲያውያን ደግሞ ለኃይለኛ ፈረሰኛ ጦራቸው ይታወቁ ነበር።


Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads