የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት

From Wikipedia, the free encyclopedia

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት
Remove ads

የመጀመሪያው የዓለም ጦርነትአውሮፓ አገሮች መኻል ከ ፲፱፻፮ ዓ/ም እስከ ፲፱፻፲፩ ዓ/ም መግቢያ፣ ለአራት ዓመታት የተካሄደ ጦርነት ነው። ይኼ ግጭት የዘመኑ ኃያላን አገራት በሁለት ተቃራኒ ወገን ተሰልፈው ያካሄዱት ግብግብ ሲሆን እስከ ሰባ ሚሊዮን ታጣቂዎች የተካፈሉበትና እስከ አስራ አምስት ሚሊዮን አውሮፓውያን ሕይወታቸውን ያጡበት ትልቅ ጦርነት ነው።

Quick facts የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት, ቀን ...
Remove ads

መነሻ

ለጦርነቱ ቅስቀሳ ብዙ ምክንያቶች በታሪክ ምሑራን ይጠቀሳሉ። ዓቢይ ከሚባሉት ነገሮች ግን የወቅቱ ኃያላን መንግሥታት የውጭ ጉዳይ ተልዕኮዎች ሲሆኑ የክብሪቱ መጫሪያ ምክንያት ግን የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያው ዘውድ አልጋወራሽአውስትሪያዊው አርች ዱክ ፍራንዝ ፈርዲናንድዩጎዝላቪያዊ ነፍሰ ገዳይ እጅ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም መገደል ነው። የሳቸውን መገደል ምክንያት በማድረግ የ አውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥትሰርቢያ ንጉዛት ሊያሟሉት የማይችሉትን፣ አስር ነጥብ ያዘለ የእላፊ ገደብ (ultimatum) ማስጠንቀቂያ ይሰጡና ገደቡ ሲያልፍ ቅድሚያውን እንደወጠኑት በሰርቢያ ላይ የጦር አዋጅ አወጁ። ይሄም የታቀደ ትንኮሳ ከአስር ዓመታት በፊት ተመሥርተው የነበሩትን ብዙ የትብብር ውሎችን የሚያንቀሳቅስ ሁኔታ ስለነበረ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሁሉንም ኃያላን መንግሥታት ጦርነቱ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስገደዳቸው። እያንዳንዳቸው ደግሞ በዓለም ዙሪያ የሚያስተዳድሯቸው ቅኝ ግዛቶች ስለነበሯቸው እነዚህንም ቅኝ ግዛቶች በዚሁ ግብግብ ተሳታፊ አደረጋቸው።

Remove ads

የጦርነቱ መግቢያ

የጦርነቱ ትርዒት የተከፈተው የአውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ሠራዊት ሰርቢያን ሲወሩ አጋራቸው የአለማኛ መንግሥት ደግሞ ቤልጂግን፣ ሉክሳምቡርግን እና ፈረንሳይን ወረረ። በተቃራኒው ደግሞ የሩሲያ ሠራዊት የምዕራብ አለማኛን ግዛት ይወራሉ። የኦቶማን ንጉሠ ነገሥት ሠራዊት ደግሞ ወዲያው ጦርነቱ ውስጥ ሲገባ በቀጣዩ ዓመት ኢጣልያቡልጋሪያ ተከትለው ገቡበት። የሩሲያ ሠራዊት ለሦስት ዓመታት ከተዋጋ በኋላ የጥቅምት አብዮት፲፱፻፲ ዓ/ም ሲፈነዳ ከዚህ ታላቅ ጦርነት ወጣ።

መጨረሻው

አለማኛ ሠራዊት በ፲፱፻፻፲ ዓ/ም የምዕራብ የጦርነቱን ግንባር ማጥቃት ከጀመሩ በኋላ የአሜሪካ ሠራዊት ከአጋሮቹ ጋር ሲሰለፍ፣ የምዕራብ አገሮች ቡድን አለማኞቹን በማጥቃት እያቸነፏቸው መጡ። መጨረሻ ላይ ተሸናፊው የአለማኛ ሠራዊት መሸነፉን አምኖ ኅዳር ፩ ቀን ፲፱፻፲፩ ዓ/ም የእጅ መስጫ ውል ሲፈርም፤ ሰኔ ፲፱ ቀን ፲፱፻፮ ዓ/ም የተለኮሰው ጦርነት አከተመ። አብሮትም የአውስትሪያ እና ሁንጋሪያ ግዛት፣ የኦቶማን ግዛት ሲጠፉ የጀርመን እና የሩሲያ ኃያልነት በፖለቲካም ሆነ በጉልበት ተደምስሰው የአራቱንም ቅኝ ግዛቶች አሸናፊዎቹ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ተከፋፈሏቸው።

የአንደኛው ዓለም ጦርነት ተስቦ

የቀድሞ ኃያላን መንግሥታትትን ውድመት ያስከተለ ክስተት ከመሆኑም ሌላ፤ በመካከለኛ አውሮፓ የብዙ ትናንሽ ሉዓላዊ አገሮችን መወለድ፤ የዓለም መንግሥታት ማኅበርን መቋቋሚያ መንስዔ፤ ከሁሉም በላይ ግን በአውሮፓ አኅጉር የብሔራዊነትን መንፈስ የቀሰቀሰና የጀርመን ሽንፈትን ያረጋገጠው የቬርሳይ ውል (Treaty of Versailles) በጀርመኖች ላይ ያስከተለው የጭቆና ስሜት አገራችን ኢትዮጵያ፲፱፻፳፰ ዓ/ም በፋሽስት ኢጣልያ በግፍ ስትወረር የተለኮሰውን የሁለተኛው የዓለም ጦርነት መነሻ ምክንያት መሆኑ ነው።

ዋቢ ምንጮች

የውጭ መያያዣ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads