አዲስ ዘመን (ከተማ)

From Wikipedia, the free encyclopedia

አዲስ ዘመን (ከተማ)
Remove ads

አዲስ ዘመንደቡብ ጎንደር የሚገኝ ከተማ ሲሆን ከባሕር ዳር ወደ ጎንደር ከተማ በሚጓዘው መንገድ መካከል ይገኛል። በድሮ ስሙ ደብረ አብርሃም ሲባል፣ በአሁኑ ጊዜ የከምከም ወረዳ አስተዳደር ማዕከል በመሆን ያገለግላል።

Quick facts

ከአዲስ ዘመን ከተማ አጠገብ ከሚገኙ ታዋቂ ቦታዎች የደብረ ገላውዲዎስ ገዳም፣ የዋሻ እንድሪያስዋሻ ተክለሃይማኖት አብያተ ክርስቲያናት እና አስባ ተራራዎች ይገኛሉ። ታሪካዊው ጉዛራም እንዲሁ በቅርብ ይገኛል። ደብረ ገላውዲዎስ በዓፄ ገላውዲዎስ ዘመን በነበረ ቅዱስ ሰው የተመሰረተ ሲሆን በቆዩ የግድግዳ ምስሎቹና ከ16ኛው ክፍለ ዘመን በሚመነጩ የወይራ ዛፎቹ ይታወቃል። በኋላ በ1572ዓ.ም. አንድ የኦሮሞ ነገድ በንጉሱ በዓፄ ሱሰንዮስ ላይ ዘመቻ ሲከፍት የዓፄ ሠርፀ ድንግል እናት ወደዚህ ቦት ደብረ አብርሃም መጥታ እንደተጠለለች ታሪክ ይዘግባል[1]

አዲስ ዘመን፣ ከ1956-1972 ዓ.ም የሊቦ አውራጃ ማዕከል በመሆንም አገልግሏል። በ1958 በተደረገ የህዝብ ቆጠራ አዲስ ዘመን ውስጥ 4400 ሰዎች የነበሩ ሲሆን፣ ከደብረ ማርቆስ የሚመጣው የስልክ አገልግሎት እዚህ ከተማ ደርሶ ነበር። በአጠቃላይ 3 ቢሮዎች እና 2 ግለሰቦች የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ ነበሩ።

Remove ads

የሕዝብ ስብጥር

More information ዓ.ም.**, የሕዝብ ብዛት ...


ማጣቀሻ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads