ኤፍሮን

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ኤፍሮን ኬጢያዊው (ዕብራይስጥ፦ עפרון החתי /ዔፍሮን ኸሔቲ/) በኦሪት ዘፍጥረት 23 ዘንድ የሰዓር ልጅ ሲሆን ከኬጢ ልጆች (ኬጥያውያን) አንድ ነበር። በመምሬከነዓን አገር ይኖር ነበር። በኬብሮን ያለውን ድርብ ክፍል የሆነውን ዋሻ ለአብርሃም ለ፬ መቶ የብር ሰቅል ሸጠው። ይህ የአብርሃም ሚስት ሣራ ባረፈችበት ጊዜ መቃብር እንዲሆንላት ነበር።

አብርሃም በዙሪያው በኩል የገነነ የከበረ ስለ ሆነ፣ የኬጢ ሰዎችና ኤፍሮንም ዋሻውን በነጻ ለአብርሃም ይሰጡት ነበር። አብርሃም ግን ባለጠጋና ጽድቅ ሆኖ ትክክለኛ ዋጋ ኢንዲከፍል ኤፍሮንን አጥብቆ ይጠይቀዋል። ይህ ዋሻ በዕብራይስጡ «መክፔላህ» ይባላል፤ ይህም «ባለ ድርብ ክፍል» ማለት ነው።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads