ኽያን

From Wikipedia, the free encyclopedia

ኽያን
Remove ads

ሰኡሰረንሬ ኽያንጥንታዊ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን15ኛው ሥርወ መንግሥት (ሂክሶስ) ፈርዖን ነበር። ስሙና ሕልውናው ከበርካታ ቅርስ ይታወቃል። ከግብጽ ውጭ ስሙ በክኖሦስቀርጤስ በክደን ላይ ከቤተመንግሥት በታች ተገኘ። እንዲሁም በደቡብ ግብጽ፣ ሐቱሳሽ ሐቲና በባቢሎን አካባቢ በመገኘቱ ንግድ ወደነዚህ አገራት እንደ ላከ ይሆናል። የእርሱ ቤተመንግሥት በቅርቡ በአቫሪስ ተገኝቷል።

==

Quick facts ሰኡሰረንሬ ኽያን, ግዛት ...

==

ማኔቶን ልማድ እንደ ተገለጸ፣ የሂክሶስ ሦስተኛ ንጉሥ «አፓሕናን» ይባላል፣ ለ36 ወይም በሌላ ቅጂ ለ63 ዓመታት ገዛ። እነዚህ ስሞች በዘመናት ላይ ከግብጽኛቅብጥኛግሪክኛና በሌሎች ልሳናት በኩል በመተረጎማቸው ቢዛቡም፣ ይህ ሦስተኛ ሂክሶስ አለቃ «አፓኽናን» እና «ኽያን» አንድ ሊሆኑ ይቻላል። ስለዚህ በግምት ዘመኑ ምናልባት 1638-1602 ዓክልበ. ያህል ሊገኝ ይቻላል።

በዮሴፉስ ቅጂ ከአፓኽናንና ከአፖፒስ በኋላ «ያናስ» የተባለ ሂክሶስ ፈርዖን ይዘረዘራል። በሥነ ቅርስ ደግሞ በአንዱ ጽላት የኽያን ልጅ ያናሢ ይጠቀሳል። ይህ ያናሢ ምናልባት አልጋ ወራሽ ቢሆንም እንደ ፈርዖን እንደ ገዛ ግን አይመስልም።


ቀዳሚው
አፐር-አናቲ
ግብፅ (ሂክሶስ) ፈርዖን
1638-1602 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሻሙቄኑ
Remove ads

ዋቢ ምንጭ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads