የካቲት ፰
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
የካቲት ፰፣ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፻፶፰ ኛው ዕለት ሲሆን፤ የበጋ ወቅት ፵፫ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፪፻፰ ዕለታት ሲቀሩ በዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፯ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፰፻፺፰ ዓ/ም - ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ የመጀመሪያውን የአቢሲኒያ ባንክ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ላይ መርቀው ከፈቱ።ከምርቃቱ ሥርዓትም በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ በቁጠባ ደብተራቸው የጠገራ ብር በባንኩ በማስቀመጥ የአዲሱ ባንክ ሁለተኛ ደምበኛ ኾኑ። የመጀመሪያው ደምበኛ በወቅቱ ለጉብኝት አዲስ አበባ ገብቶ የነበረው እንግሊዛዊው አርኖልድ ሄንሪ ሳቬጅ ላንዶር (Arnold Henry Savage Landor) ነበር። [1]
- ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - በሆለታ ገነት፣ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ስም የጦር ተማሪ ቤት ተከፈተ።
- ፲፱፻፵፬ የታላቋ ብሪታኒያ የንግሥት ኤልሳቤጥ አባት ንጉሥ ጆርጅ ሳድሳዊ በዊንድሶር ግምብ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት ውስጥ ተቀበሩ።
Remove ads
- ፲፱፻፶፬ ዓ/ም - እቴጌ መነን አስፋው በዚህ ዕለት በተወለዱ ፸፫ ዓመታቸው አረፉ።
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads