1944

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

1944 አመተ ምኅረት

  • ጥቅምት ፲፮ ቀን - በብሪታንያ ብሔራዊ ምርጫ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስቴር በነበሩት በዊንስተን ቸርቺል የሚመራው የኮንሰርቫቲቨ ፖለቲካ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቸርቺልም ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆኑ።
  • ታኅሣሥ ፪ ቀን - የአንበሳ አውቶቡስ ህጋዊ ሰውነት በማግኘት በአክሲዮን ከተቋቋመ በኋላ አረንጓዴና ቢጫ የተቀቡ ፲ አውቶቡሶችን ይዞ ሥራ ጀመረ፤ እነዚህም አውቶቡሶች በከተማዋ አራት መስመሮች ላይ ብቻ የተሰማሩ ነበሩ።
  • ታኅሣሥ ፲፬ ቀን - እስከ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኢጣልያ ቅኝ ግዛትነት፡ እስከነጻነት ደግሞ በብሪታንያ እና ፈረንሳይ ሥር የነበረችው ሊቢያ ነጻ ሆነች። 1 ኢድሪስ የሊብያ ንጉሥ ሆኑ።
  • ጥር ፲፫ ቀን - ለአዲስ አበባ ሕዝብ የውሃ አገልግሎት የሚሰጠው የገፈርሳ ግድብ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ተመረቀ።
  • የካቲት ፩ ቀን - በታላቋ ብሪታኒያ እና ሰሜን አየርላንድ ንጉዛት ልዕልት ኤልሳቤጥ አባታቸው ንጉሥ ጆርጅ ሳድሳዊ ሲያርፉ ዙፋኑን ተቀብለው ዳግማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ሆኑ።
  • የካቲት ፰ ቀን - የብሪታንያ ንጉሥ ጆርጅ ሳድሳዊ በዊንድሶር ግምብ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት ቤት ውስጥ ተቀበሩ።
  • ሚያዝያ ፫ ቀን - የአዲስ አበባው ሊሴ ገብረ ማርያም ትምሕርት ቤት ተመረቀ።
  • ሚያዝያ ፳፬ ቀን - ‘ደ ሀቪላንድ-ኮሜት’ የተባለው የዓለም የመጀመሪያው የተሳፋሪ ጄት አየር-ዠበብ የመጀመሪያ በረራውን ከሎንዶን እስከ ጆሃንስበርግ ድረስ አከናወነ።
  • ሐምሌ ፲፮ ቀን - በጋማል አብደል ናስር የተመሠረተው የግብጽ የመኮንኖች እንቅስቃሴ በጄነራል ሙሐመድ ናጊብ መሪነት ንጉሥ ፋሩቅን ገለበጠ።
  • ሐምሌ ፲፱ ቀን - የግብጽ ንጉሥ ፋሩቅ ዙፋናቸውን ለልጃቸው ንጉሥ ፉዋድ ለቀቁ።
  • ነሐሴ ፭ ቀን - በዮርዳኖስ ሐሺሚ ንጉዛት ንጉሡ ታላል በአዕምሮ ሕመምተኛነት ምክንያት በአገሪቱ ምክር ቤት ሸንጎ «ለሥልጣን ብቃት የላቸውም» ተብለው ሲሻሩ ገና አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ልጃቸው አልጋወራሹ በንጉሥነት እንደተኳቸው ይፋ ተደረገ። ንጉሥ ሁሴን የልደታቸው ዕለት ኅዳር ፯ ቀን ፲፱፻፵፮ ዓ/ም የንግሥ ስርዓታቸው ተከናወነ።
Quick facts
Remove ads

ልደቶች

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads