ጀድኸፐረው
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ጀድኸፐረው ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ለአጭር ጊዜ በ1781 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ። የሰኸምሬኹታዊ ኻውባው ተከታይ ነበረ።
==
==
ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ላይ የለም። ሆኖም ከሥነ ቅርስ ረገድ ፈርዖንነቱ እርግጥኛ ነው። ስሙ ከቶሪኖ ዝርዝር ጠፍቶ የኻውባው ተከታይና ወንድም እንደ ነበር ይታስባል፤ በ«ኦሲሪስ አልጋ» በተባለው ቅርስ ላይ ሌላ ስሙ (የአባት ስም) «ሆር» (ሆር አዊብሬ) እንደ ነበር ይመስላል። በተጨማሪ የጀድኸፐረው ስም በ፲፩ ማኅቴሞች ላይ በአባይ ፪ኛው ሙላት አካባቢ (በኩሽ መንግሥት ጠረፍ) ሲገኝ ማኅተሞቹ ከቀዳሚው ከኻውባውና ከታችኛው ግብጽ ፈርዖን ከሸሺ ማዓይብሬ ማኅተሞች አጠገብ ተገኙ።
የጀድኸፐረው ተከታይ ሰጀፋካሬ (ካይ-አመነምሃት) ምናልባት ልጁ ነበር።
ቀዳሚው ሰኸምሬኹታዊ ኻውባው |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ሰጀፋካሬ |
Remove ads
ዋቢ ምንጭ
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads