ጅን አሰገድ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
አጼ ጅን አሰገድ የአጼ ይግባ ጽዮን ልጅ የአጼይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅ ሲሆኑ ከ1297-1298 ለአንድ አመት የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። ታሪክ ጻህፍት እንደሚሉት አባታቸው ይግባ ጽዮን 5 ወንድ ልጆች ስለነበሩዋቸውና የትኛው ንጉስ እንዲሆን መምረጥ ስላልቻሉ እያንዳንዱ ወንድ ልጅ አንድ አንድ አመት እንዲነግስ ቃል ስላስገቡዋቸው 1 አመት ብቻ ነግሰዋል[1] [2]
ዋሊስ በድጅ የተሰኘው የታሪክ ተመራማሪ ተፎካካሪ የንጉሳዊ ቤተሰቦችን አምባ ግሸን ማሰር የጀመሩት እኒሁ ንጉስ ናቸው ይላል። ይህንም ያደረጉት አስቸጋሪ ወንድማቸውን ሳባ ሰገድን ከራሳቸው ለማራቅ ነበር ይላል ዋሊስ። ከሳባ ሰገድ በተጨማሪ ሶስቱ ወንድሞቻቸውንና የራሳቸውን ልጅ አምባው ላይ እንዳሰሩ ዋሊስ ያትታል።[3]
ሆነም ቀረም ጅን አሰገድ የነገሱት ለአንድ አመት ብቻ ነበር።
Remove ads
ማጣቀሻወች
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads