ግመል

From Wikipedia, the free encyclopedia

ግመል
Remove ads

ግመል ሙሉ ጣት ሸሆኔ ካላቸው እንስሳ የሚመደብ ለማዳ የቤት እንስሳ ወገን ነው። በዋነኛነት ጀርባው ላይ ባለው በስብ የተሞላ አካል (ሻኛ) ይታወቃል። ይህ ሻኛ የአረቦች ግመል በሚባለው ዝርያ ላይ አንድ ብቻ ሲሆን፣ ሌላው ዝርያ በሰሜን ምስራቅ እስያ የሚገኘው ባክትሪያን ግመል ደግሞ ሁለት ነው። በአብዛኛው ደረቅ በረሀ ለመኖር የሚመቻቸው ሲሆን በብዛት በምዕራብ እስያ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ እስያ ይገኛሉ። የሠው ልጅ የሚያለምዳቸው ለወተት ምርት፣ ለስጋ፣ ለግመል ጽጉር ልብስ (በተለይ ከባክትሪያን ግመል) እንዲሁም አልፎ አልፎ ለመጓጓዣ ስለሚጠቅሙ ነው።

ለፊደሉ፣ ገምልን ይዩ።
Thumb

የግመል ወተት በብዙ አገራት ይገዛልና ይጠጣል። በአረቢያዩናይትድ ኪንግደምሶማሊያሞሪታኒያአሜሪካ በሱቅ ይሸጣል። የግመል ወተት የሚያስገኙ ዋና አገራት ሶማሊያኬንያማሊኢትዮጵያኒጄርሳዑዲ አረቢያ፣ እና ሱዳን ናቸው።

የግመል ሥጋ ደግሞ ለብዙ አገራት ምግብነት ከፍ ያለ ዋጋ አለው። በተለይ የግመል ሥጋ የሚበላው በኤርትራኢትዮጵያሶማሊያጂቡቲሱዳንግብጽሊብያሶርያ፣ አረቢያና ካዛክስታን ይበላል።

Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads