ፎገራ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ፎገራ
Remove ads

ፎገራ በደቡብ ጎንደር የሚገኝ ወረዳ ሲሆን፣ የወረዳው አስተዳደር ማዕከል ወረታ ይሰኛል። በዚህ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ታዋቂ ትናንሽ ከተሞች ውስጥ አመድ በር እና አውራአምባ ይገኛሉ።


Thumb

የፎገራ ወረዳ መሬት ይዞታ ባሕርይ[1]

  ሊታረስ እሚችል (44.2%)
  በመስኖ የለማ (20%)
  ግጦሽ (22.9%)
  ደን (1.8%)
  በውሃ የተሸፈነ (3.7%)
  ሊለማ እማይችል (7.4%)

ጉማራ እና ርብ ወንዝ ይህን ክፍል ሲያካልሉት ለጣና ሐይቅ ያለው ቅርበት ደግሞ የውሃ ሃብቱን ያጎላዋል። 490 ስኩየር ኪ.ሜ. እሚያክለው የዚህ ወረዳ መሬት በየአመቱ በጣና ሐይቅ ሙላት ምክንያት የጎርፍ ተጠቂ ነው። [2] ጤፍማሽላዳጉሳጥጥሰሊጥ ዋናዎቹ የዚህ ወረዳ ምርቶች ናቸው። የፎገራ ላም ለየት ያለ የላም ዝርያ ዓይነት ሲሆን በግዙፍነቱና በከፍተኛ የወተት ምርቱ ይታወቃል። ሆኖም በበጋ ወራት ከከምከም እና ደራ ወረዳዎች ላሞች ወደዚህ ወረዳ ለግጦሽ ስለሚመጡ የዚህ ዝርያ ላም በመዳቀል ኅልውናው አስጊ ሆኗል።

ፎገራ የአለቃ ገብረሃና የትውልድ ቦታ በመሆኑም ይታዎቃል።

Remove ads

የሕዝብ ስብጥር

More information ዓ.ም.**, የሕዝብ ብዛት ...


ማጣቀሻ

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads