1 ነፈርሆተፕ

ስለ ፍቅር From Wikipedia, the free encyclopedia

1 ነፈርሆተፕ
Remove ads

1 ነፈርሆተፕ ኻሰኸምሬ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1701 እስከ 1690 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የ3 ሶበክሆተፕ ተከታይ ነበረ።

==

Quick facts ነፈርሆተፕ ኻሰኸምሬ, ግዛት ...

==

ቶሪኖ ቀኖና ዘንድ ኻሰኸምሬ ነፈርሆተፕ ለ፲፩ ዓመት ገዛ ሲለን ለእርሱ ብዙ ሐውልቶችና ቅርሶች ይታወቃሉ። እንደ ቀዳሚው ፫ ሶበክሆተፕ ከወታደራዊ ቤተሠብ እንደ መጣ ይመስላል። አባቱ ሀዓንኸፍና እናቱ ከሚ ነበሩ፤ የዚህም ሀዓንኸፍ አባት ነሂ እናቱም ሰነብቲሲ ተባሉ። ይህም ነሂ «የከተማ ሻለቃ» የሚመስል ማዕረግ እንደ ነበረው ይታወቃል። የሀዓንኸፍ ፫ ልጆች ሁሉም ፈርዖኖች ስለ ሆኑ በበርካታ ጽላቶች ይከበራል። የነፈርሆተፕ ልጆች ደግሞ ልዑል ሀዓንኸፍና ልዕልት ከሚ ተባሉ።

ጌባል (በፊንቄ) የተገኙት ቅርሶች የነፈርሆተፕ «አገረ ገዥ» በጌባል «ያንቲኑ» እንደ ነበር ያስረዳሉ። እሱም ከማሪ ጽላቶች ያንቲን-ዓሙ «የጌባል ንጉሥ» ይባላል። ይህም ነፈርሆተፕ በባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ዘመን እንደ ነገሠ ማስረጃ ነው።

Thumb
የ፩ ነፈርሆተፕ ምስል

ወደ ነፈርሆተፕ ዘመን መጨረሻ ወንድሙ ሲሐጦር ከእርሱ ጋራ የጋርዮሽ ፈርዖን ተደርጎ ሲሐጦር በጥቂት ወራት ውስጥ እንደ ሞተ ይመስላል፤ ከዚያም ሌላ ወንድማቸው ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ የጋርዮሽ ፈርዖን ሆነ። ከዚያም ትንሽ በኋላ ነፈርሆተፕ ዓርፎ ካነፍሬ ሶበክሆተፕ ለብቻ ፈርዖን ሆነ።

ቀዳሚው
3 ሶበክሆተፕ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን ተከታይ
ካነፈሬ 4 ሶበክሆተፕ
Remove ads

ዋቢ ምንጭ

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads