2 ቱትሞስ

From Wikipedia, the free encyclopedia

2 ቱትሞስ
Remove ads

፪ ቱትሞስ (ግብጽኛ፦ /ጀሁቲመስ/) ዓኸፐረንሬጥንታዊ ግብጽግብጽ አዲስ መንግሥትና የ18ኛው ሥርወ መንግሥት ፈርዖን ሲሆን ምናልባት 1501-1487 ዓክልበ. የገዛ ነበረ።

==

Quick facts ቱትሞስ ዓኸፐረንሬ, ግዛት ...

==

2 ቱትሞስ የቀዳሚው የ1 ቱትሞስና የንግሥቱ ሙትኖፍረት ልጅ ነበር። የ2 ቱትሞስ ዋና ንግሥት ደግሞ ያባቱና የሌላይቱ ንግሥት አሕሞስ ልጅ ሃትሸፕሱት ነበረች። የ2 ቱትሞስ ቁባት ንግሥት ኢሰት ተባለች፣ እርሷም የተከታዩ 3 ቱትሞስ እናት ሆነች።

ማኔጦን መሠረት ለ13-14 ዓመት እንደ ገዛ ባብዛኛው ይቀበላል። አንዳንድ መምህሮች ግን ዘመኑ ከ3-4 አመት በላይ አይሆንም ይላሉ።

በ፪ ቱትሞስ ዓኸፐረንሬ ዘመን አባቱ ከኩሽ መንግሥት የያዛቸው የኖቢያ ግዛቶች ያምጹበት ነበር፤ እሱ ግን ሥራዊቱን ልኮ አስመለሠው።

የጦር አለቃው አሕሞስ ፐን-ነኽበት ደግሞ «ሻሱ» በተባለ ወገን ላይ ዘምቶ በርካታ ምርከኞች እንደ ያዘ ይላል። እነኚህ በደቡብ ከነዓን የተገኙት የኤዶምያስ ሰዎች ወይም ሌሎች እንደሚሉ ዕብራውያን ነበሩ። በተጨማሪ ሌላ የተገኘ ጽሑፍ እንዳለን ዓኸፐረንሬ በረጨኑ (ሶርያ) እስከ ኒይ ከተማ ድረስ ዘመተ። ወደ ሶርያ የደረሱ በመርከብ ወይም በመሬት እንደ ሆነ አልተገለጸም።

የ፪ ቱትሞስ ተከታይ በይፋ ልጁ ፫ ቱትሞስ ሲሆን እሱ ግን ገና ሕጻን ልጅ ሆኖ የቱትሞስ ንግሥት ሃትሸፕሱት ባለሙሉ ሥልጣን እንደራሴው፣ በቅርብም ጊዜ ውስጥ በራስዋ መብት ፈርዖን ተባለች። በ22ኛ ዓመትዋ (1466 ዓክልበ. ግ.) ዓርፋ ያንጊዜ ፫ ቱትሞስ ለብቻው ፈርዖን ሆነ።

ቀዳሚው
1 ቱትሞስ
ግብፅ ፈርዖን
1501-1487 ዓክልበ.
ተከታይ
ሃትሸፕሱት
Remove ads
Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads