3 ነፈርሆተፕ
From Wikipedia, the free encyclopedia
Remove ads
ሰኸምሬ ሳንኽታዊ 3 ነፈርሆተፕ በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) ምናልባት 1637-1636 ዓክልበ. አካባቢ የገዛ ፈርዖን ነበረ።
==
==
ስሙ «ሰኸምሬ ሳንኽታዊ ነፈርሆተፕ» የሚታወቀው ከአንድ ቅርስ ብቻ ነው። ይህ ጽላት በጣም የተጎዳ ቢሆንም «የጤቤስ ንጉሥ» እንደ ነበር ይገልጻል። ብስሙ ውስጥ «ታዊ» ቢገኝም፣ ይህ በሂክሶስ ዘመን ስለ ነበር፣ እንዲሁም አቢዶስ በአቢዶስ ሥርወ መንግሥት ነጻ እንደ ሆነ ስለሚታሰብ፣ 3 ነፈርሆተፕ በእውነት በታችኛ ግብጽ ላይ እንደ ገዛ አይታሰብም።
ከዚህ በቀር በቶሪኖ ቀኖና ላይ በአንድ ክፍል «ሰኸምሬ ፫ አመት፣ ሰኸምሬ ፲፮ አመት፣ ሰኸምሬ... ፩ አመት» ሲል ይህ ክፍል ባብዛኛው የ16ኛው ሥርወ መንግሥት እንደ ሆነ ይታመናል። ሦስተኛው የተዘረዘረው ለ፩ አመት የገዛው ሰኸምሬ 3 ነፈርሆተፕ እንደ ነበር ይገመታል።
ቀዳሚው 8 ሶበክሆተፕ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1637-1636 ዓክልበ. ግድም |
ተከታይ መንቱሆተፒ |
Remove ads
Wikiwand - on
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Remove ads