መስከረም ፳፮

From Wikipedia, the free encyclopedia

Remove ads

ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፳፮ኛው ዕለት እና የመፀው የመጀመሪያው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፵ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፱ ዕለታት ይቀራሉ።

መስከረም ፳፮

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች "ዘመነ ጽጌ" ወይም "ወርኅ ጽጌ" የሚባለውን የማርያምን ስደት መታሰቢያ የ ፵ ቀን የጽጌ ፆም በዛሬው ዕለት ጀምረው ኅዳር ፮ ቀን ይፈቱታል።

ታሪካዊ ማስታወሻዎች

፲፰፻፹፪ ዓ/ም -ቶማስ ኤዲሶን የተባለው አሜሪካዊ የፈጠራ ሰው የመጀመሪያውን ተንቀሳቃሽ ምስል (motion picture) አሳየ።

፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የግብጽ ሠራዊት በእስራኤል ላይ የ’ረመዳን ጦርነት’ ወይም የ’ዮም ኪፑር’ ጦርነት በመባል የሚታወቀውን የስድስት ቀን ውጊያ ከፈቱ።

፲፱፻፸፬ ዓ/ም - የግብጽ አመጸኛ መኮንኖች ፕሬዚደንታቸውን አንዋር ሳዳትን አደባባይ ላይ በጥይት ደብድበው ገደሏቸው።

ልደት


ዕለተ ሞት

፲፬፻፬ ዓ/ም - በ፲፫፻፸፭ ዓ/ም በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ ተቀምጠው ለሃያ ዘጠኝ ዓመት የነገሡትና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ግማደ መስቀል ወደኢትዮጵያ ያስመጡት ዳግማዊ ዓፄ ዳዊት ፈረሳቸው ረግጧቸው ሞቱ። [1]

፲፱፻፸፬ ዓ/ም የኖቤል የሰላም ሽልማት ተቀባይ እና የግብጽ ሦስተኛው ፕሬዚደንት አንዋር ሳዳት በአመጸኛ መኮንኖች እጅ ተገደሉ።

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads