ከበደ ሚካኤል

From Wikipedia, the free encyclopedia

ከበደ ሚካኤል
Remove ads

ከበደ ሚካኤል፤ ህዳር ፪ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. ተወለደ – ህዳር ፲፪ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. አረፈ) በኢትዮጵያዊ ተወላጅ የልቦለድ እና ልቦለድ ያልሆኑ ሥነ-ጽሑፍ ደራሲ ነበር። በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት አዋቂ እና ሁለገብ ምሁራን አንዱ ነው ተብሎ የሚታሰበው - ገጣሚ፣ ፀሐፌ ተውኔት፣ ድርሰት፣ ተርጓሚ፣ ታሪክ አዋቂ፣ ደራሲ፣ ፈላስፋ፣ ጋዜጠኛ እና የመንግስት አገልጋይ ነበር። እርሱም የሸዋ አማራ መኳንንት እና የሰለሞናዊ ስርወ መንግስት አባል ሲሆን የእናት ቅድመ አያታቸው የሸዋ ንጉስ ሳህለ ሥላሴ ነበሩ። በተለያዩ ቋንቋዎች ወደ ዘጠና የሚጠጉ የታተሙ ሥራዎችን አዘጋጅቷል፤ አንዳንዶቹም ወደ ውጭ ቋንቋዎች ተተርጉመዋል። በሃያኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ እና ምሁራዊ አስተሳሰብ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪን ጨምሮ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝተዋል። የመጀመሪያ ሕይወት እና ትምህርት ከበደ ሚካኤል በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ገሪም ገብርኤል ከአቶ አይታገድ እና ከወይዘሮ አፀደ ሚካኤል ህዳር ፪ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. ተወለደ። ከተወለደ በኋላ ብዙም ሳይቆይ አባቱ ከአገሩ ወጥቶ በመጥፋቱ፣ በእናቱ የመጨረሻ ስም ይታወቅ ነበር። አጎቱ ልጅ ሰይፉ ሚካኤል የአባታቸው አባት ሆነው ወደ ጉልምስና ያሳድጉት ነበር። ከበደ ሚካኤል ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ተከታትሏል። በአራት ዓመቱ በአያታቸው በደጃዝማች መኩሪያ ተስፋዬ በተመሰረተው በአቅራቢያው በሚገኘው ገሪም ገብርኤል ቤተክርስቲያን የቤተክርስቲያን ትምህርቱን ጀመረ። በዘጠኝ ዓመቱ ብዙ የቤተ ክርስቲያንን ትውፊታዊ ትምህርት ተምሮ የቤተክርስቲያንን ቋንቋ ግእዝን በሚገባ ተምሮ ነበር። በ፲፱፻፳፬ ዓ.ም. እናቱ እና አያቱ ለሥራ ወደ አሩሲ ሲሄዱ፣ እርሱም አዲስ አበባ ወደሚገኘው አጎቱ ልጅ ሰይፉ ሚካኤል በመሄድ የካቶሊክ ካቴድራል ትምህርት ቤትን በአዳሪ ተማሪነት ተቀላቀለ። እናቱ በ፲፱፻፳፱ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። በወቅቱ የኢትዮጵያ ምርጥ አዳሪ ትምህርት ቤት በሆነው በአሊያንስ ኤቲዮ-ፍራንሴስ ት/ቤት በአጎታቸው እርዳታ ተመዘገበ። በወቅቱ የ ፲፫ ዓመት ወጣት የነበረው ከበደ ሚካኤል፣ አጎቱ የሀረርን ክፍል Bold textእንዲያስተዳድሩ በተሾሙበት ወቅት፣ ልዑል መኮንንን በማስተማር ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር። ስለ ከበደ ሚካኤል ህይወት እና ሥራ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይፈልጋሉ?

Quick facts ሙሉ ስም, የትውልድ ቀን ...

ከበደ ሚካኤል 30 ገደማ መፃሕፍትን ፅፈዋል። ከበደ ሚካእል ካበረከቷቸው የቴአትር ስራዎች

ይገኙባቸዋል።

ከበደ ሚካኤል በርካታ የስነ ጽሁፍ ስራዎች ባለቤት በመሆናቸው በተለይም ለልጆች ትምህርት አዘል ጽሁፎችን የግጥም የፈጠራ ስራዎችን ቅኔዎችን በስፋት በማበርክታቸው በኢትዮጵያ የስነጽሁፍ መድረክ ገናና ከሆኑት ደራሲዎች አንዱ ናቸው። ከነዚህም መሃል፦

  • ታሪክና ምሳሌ ፩
  • የህሊና ብርሃን
  • የቅኔ ውበት (በ ......... ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
  • ጃፓን እንዴት ስለጠነች (በ ....... ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
  • ታላላቅ ሰዎች (በ ........ ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
  • የሥልጣኔ አየር (በ ......... ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)

ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የሰዎች ስነ ምግባር ላይ የማተኮርና ምክር አዘል መልእክቶችን የማስተላለፍ ዝንባሌአቸው በአብዛኛው ስራቸው ላይ ይንጸባረቃል።

ዘመናዊት ኢትዮጵያን ለማደርጀት በተደረገው ትግል በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ እኒህ ፈላስማ፥ ባለቅኔ፥ ጸሐፌ-ተውኔት፥ ደራሲና አንጋፋ ጋዜጠኛ ፥ 'የቀለም ሰው' በሀገራችን የመጀመሪያ የነበረውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት በቀዳሚነት የተቀበሉ ሲሆን፣ አዲስ ትውልድ ላፈራ ስብእናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክቶሬት ዲግሪ ሸልሟቸዋል። በተረፈም ከፈረንሳይጀርመንሶቭየት ህብረትሜክሲኮ ሽልማትን ተቀብለዋል።

በተረፈ የትምህርት ሚኒስትር ዳይረክተር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተከታይ ዳይሬክተር (፲፱፵፪)፣ የብሄራዊ መጻህፍት ቤት ዳይረክተር (፲፱፵፬)ና የካቢኔ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል።

ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል፥ ኢትዮጵያዊ 'የቀለም ሰው' ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. በሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።[1]

Remove ads

ናሙና ግጥሞች


የተማረ ሆኖ እውነቱን የማይገልጽ ፣
ባለ ጸጋ ሆኖ ገንዘቡን የማይሰጥ፣
ደሃ ሆኖ መስራት የማይሻ ልቡ፣
ሶስቱም ፍሬ ቢሶች፣
ለምንም አይረቡ።

አይነ የለውም አሉ የሰነፍ ልመና
ወደ አምላክ ሲጸልይ ማታ በልቦና
መንገዱ ሳይመታኝ ባቧራ በጭቃ
አድርገኝ ይለዋል ላገሬ እንድበቃ
እንጦጦ ተኝቼ ሃረር እንድነቃ

መርዝም መድሃኒት ነው ሲሆን በጠብታ
እንዲሁም ለተንኮል አለው ቦታ ቦታ
ምን ቢሰለጥኑ ቢራቀቁ በጣም
ሁልጊዜ ደጋግሞ ብልጠት አያዋጣም።
በጅ የተበተቡት ተንኮል ዞሮ ዞሮ
ማጋለጡ አይቀር እጅና እግር አስሮ ።
መጽሓፉም ይለናል ሲያስተምረን ጥበብ
ብልጥ ሁን እንደባብ የዋህ ሁን እንደርግብ
ስለዚህ በብልጠት ተንኮል ስትሰሩ
በዝቶ እንዳይገላችሁ ገርነት ጨምሩ ...
የዕውቀት ብልጭታ የተወሰደ
Remove ads

ዋቢ ምንጮች

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads