From Wikipedia, the free encyclopedia
ኒል አርምስትሮንግ አሜሪካዊ የህዋ መንኩራኩር አብራሪ ሲሆን በጁላይ 20፣ 1969 እ.ኤ.አ. በአፖሎ ፲፩ የመንኩራኩር ጉዞ ጨረቃ ላይ በመራመድ የመጀመሪያ የሰው ልጅ ነው። ይህ በጣም ጎበዝ ሥራ ነው። ናሳን እ.ኤ.አ በ1962 ከመቀላቀሉ በፊት የአሜሪካ ባህር ሃይል ውስጥ የተዋጊ ጀት አብራሪ ሆኖ በኮሪያ ጦርነት ወቅት ተሳትፎ ነበር። ናሳን ተቀላቅሎ ከአራት አመት በኋላ ወደ ህዋ የመጀመሪያውን ጉዞ ያደረገ ሲሆን በዛም ጉዞ የመጀመሪያውን በሰው ልጅ የታገዘ የመንኩራኩሮች መያያዝ አከናውኗል። ከዚህ ጉዞው በኋላ ወደ ህዋ ያልሄደው ኒል በተወለደ በ 82 አመቱ በኦገስት 26፣ 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። [1]
በሐምሌ ፳፱ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ.ም. (ኦገስት 5, 1930 እ.ኤ.አ.) በኦሃዮ ክፍላገር፣ አሜሪካ የተወለደው ኒል አርምስትሮንግ ከወላጆቹ እና እሱን ጨምሮ ሶስት ልጆች ባሉበት ቤተሰብ ውስጥ አደገ።
ከውትድርና በኋላ ወደ ኮሌጅ ገብቶ ትምህርቱን የተከታተለው ኒል ከተመረቀ በኋላ ለምርምር ፕሮግራሞች ሞካሪ አብራሪ ለመሆን ተመዝግቦ እ.ኤ.አ በJuly 1955 ተሳክቶለት ስራ ጀመረ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.