![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/4/46/%25E1%258A%25A0%25E1%2589%25A1%25E1%258A%2590_%25E1%258B%25AE%25E1%2588%25B4%25E1%258D%258D_%25E1%2589%25B0%25E1%2588%25AB%25E1%2588%25AB.png/640px-%25E1%258A%25A0%25E1%2589%25A1%25E1%258A%2590_%25E1%258B%25AE%25E1%2588%25B4%25E1%258D%258D_%25E1%2589%25B0%25E1%2588%25AB%25E1%2588%25AB.png&w=640&q=50)
አቡነ ዮሴፍ ተራራ
From Wikipedia, the free encyclopedia
አቡነ ዮሴፍ ተራራ ከላሊበላ በስተስሜን ምስራቅ የሚገኝ፣ ከኢትዮጵያ በከፍታው 16ኛ የሆነ ተራራ ነው። ከባህር ወለል በላይ 4260ሜትር የሚደርሰው ይህ ከፍተኛ ቦታ ከአካባቢው ጠለል ደግሞ በ1909 ሜትር ወደላይ ይጎናል። አቡነ ዮሴፍ ተራራ መቼና መድኃኔ አለምን፣ይምርሃነ ክርስቶስን፣ ጀመዱ ማርያምን፣ ገነተ ማርያምን፣ አሸተን ማርያምንና ሌላ አንድ የአለት ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናንን በማቀፍ በታሪክ ይታወቃል። የእንግሊዙ አርኪዮሎጂ ተማሪ ክራውፎርድ የጨረቃ ተራራ ተብሎ በጥንቶቹ ግሪኮችና አረቦች የሚታወቀው ጀበል ኤል-ካማር ይህ ተራራ እንደነበር ያስረዳል[1]። የጨረቃ ተራራ (ጀበል ኤል ካማር) በኋላ ኢኩየተር በመባል ለምድር ወገብ ስሙን የለገሰ ሐረግ ነው።