ወልደያ
ወልደያ / From Wikipedia, the free encyclopedia
ወልደያ ወይንም ወልዲያ ከደሴ ሰሜን 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከላሊበላ ደግሞ በደቡብ ምስራቅ ያለ በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ከተማ ሲሆን በሰሜን ወሎና በወልዲያ ወረዳ ይገኛል። ከኢኮኖሚ አንጻር ለሕንጻ ስራ የሚያገለግል የኖራ ምርት በአካባቢው በትንሹ መካሄዱ በታሪክ ይጠቀሳል[1]።
Quick Facts
Close
ወልድያ ከተማ በ1770ዎቹ በታላቁ ራስ ዓሊ የንግሥና ዘመን የተመሰረተች፤ 4 ዋና ዋና የአውራ ጎዳና መንገዶች የሚገናኙባት ለአብዛሃኛው የሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች መገናኛ ከተማ ነች፡፡
ወልድያ
ወልድያ ከተማ በ1770ዎቹ በታላቁ ራስ ዓሊ የንግሥና ዘመን የተመሰረተች፤ 4 ዋና ዋና የአውራ ጎዳና መንገዶች የሚገናኙባት ለአብዛሃኛው የሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች መገናኛ ከተማ ነች፡፡ መገኛነቷን ስንቃኝም ከአዲስ አበባ 520 ኪ.ሜ፣ ከባህር ዳር 360 ኪ.ሜ፣ ከላልይበላ 168 ኪ.ሜ፣ ከመቀሌ 260 ኪ.ሜ፣ ከጅቡቲ ወደብ (በአፋር በኩል) 553 ኪ.ሜ እርቀት የተነሱ ሁሉ የሚገናኙባት ናት፡፡ በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት የራስ ወሌ ብጡል ቤተ-መንግሥት በነበረበት በመርጦ አቅጣጫ እዜት በርን አቋርጦ በመገንባት ላይ ያለው የደላንታ መንገድም ከተማዋን በማማከል 5ኛ ሀገር አቋራጭ መንገድ መሃል ከተማዋን ያቋርጣል፡፡