ደሴ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ደሴ በወሎ ክፍለ ሃገር የሚገኝ ከተማ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የደቡብ ወሎ ዋና ከተማ ነው። የወይና ደጋ አየር ጸባይ ያለው ይህ ከተማ፣ በከተማነት ታዋቂ እየሆነ የመጣው በዓፄ ዮሐንስ ፬ኛ ዘመን እንደሆነ ይጠቀሳል። የአካባቢው መሬት ከእሳተ ጎሞራ ቅሪት የሚመነጭ ስለሆነ፣ በንጥረ ነገር የዳበርና ለምነት ስለሚያሳይ፣ ከተማው በ20ኛው ክፍለዘመን በፍጠነት እንዲያድግና በኋላም በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እና ደርግ ዘመን ወሎ ተብሎ ለተሰየመው ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ እንዲሆን ዋና አስተዋጽዖ አድርጓል[1]።
Quick Facts
ደሴ | |
ፒያሳ ከሰሜን ወደ ደቡብ ያለው እይታ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | አማራ ክልል |
ዞን | ደቡብ ወሎ |
ከፍታ | 2470 ሜትር |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 170,000 (ግምታዊ) |
Close