M
From Wikipedia, the free encyclopedia
M / m በላቲን አልፋቤት አሥራ ሦስተኛው ፊደል ነው።
More information ግብፅኛ ነ, ቅድመ ሴማዊ ሜም ...
Close
More information የላቲን አልፋቤት, ተጨማሪ ምልክቶች፦ ...
Close
የ«M» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ሜም» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የውሃ ማዕበል ስዕል መስለ። የግብጽኛ ተናባቢ ድምጽ ምልክቶች በሚል ጽሕፈት ለዚህ ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ለድምጹ «ነ» ነበር፤ በሴማውያን ዘንድ ግን «ም» ሆነ። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ከዚህም በግሪክ አልፋቤት "ሙ" (Μ, μ) ደረሰ።
ከ600 ዓክልበ. ግድም በፊት፣ በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት እንዲሁም በጥንታዊ ኢታሊክ አልፋቤት ሌላ ፊደል 𐌑 ለ«ሥ» ጠቀመ፤ የ«ም» ቅርጽም እንደ «𐌌» ይምሰል ነበር። የ𐌑 (ሥ) ጥቅም በ600 ዓክልበ. ግድም ጠፋ፤ ከዚያስ በ400 ዓክልበ. ግድም የ«𐌌» (ም) ቅርጽ እንደ ዛሬ M ለመምሰል ጀመረ።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «መ» («ማይ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ሜም» ስለ መጣ፣ የላቲን 'M' ዘመድ ሊባል ይችላል።