From Wikipedia, the free encyclopedia
አመድ በር በአሞራ ገደል እና ደብረ ታቦር መካከል የምትገኝ በፎገራ ወረዳ ስር ያለች ትንሽ ከተማ ናት። አመድ በር ውስጥ፣ እንደ 2005 ህዝብ ቆጠራ፣ 5፣ 517 ሰዎች ይኖራሉ። [1]
አመድ በር | |
ከፍታ | 2691 ሜ |
የሕዝብ ብዛት | |
• አጠቃላይ | 5517 |
እቴጌ ሰብለ ወንጌል 1560 ዓ.ም. አመድ በር ላይ እንዳረፈች ይጠቀሳል። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ነገሥታቱ ክረምትን በ አመድ በርና በአካባቢው በሚገኙት አሪንጎና ቃሮዳ ያሳልፉ እንደንበር ዜና መዋዕላቸው ያትታል። ይሄውም እንደይባባ፣ አይባ፣ እንፍራዝ፣ ጣዳ፣ ወይናረብ፣ መንዘሮ ወዘተ መሆኑ ነው [2][3]። ሐዋርያ የተሰኘው የአምባሰል መሪ በዣንጥራር ተስፋ እየሱስ ተይዞ እንዲመጣ ታላቁ እያሱ የላከው ከዚሁ ከአመድ በር ነበር [4]።
በ1769ዓ.ም. ራስ አሊ] የሚመራው ከላስታ፣ አምባሰልና ዋግ የተሰባሰበ የየጁ ፈረሰኛ በአንድ ጎን፣ በወልደ ገብርኤል የሚመራው መድፍና ጠመንጃ የታጠቀ ከሰሜን፣ ደምበያ፣ ትግሬና ጎጃም የተሰባሰበ የክርስቲያን ክፍል በሌላ ጎን፣ ከፍተኛ ጦርነት አድርገው የጁዎች ጦርነቱን ያሸነፉበት ቦታ ነው። ይህ የአመድ በር ጦርነት ሽንፈት በጎንደር ከተማ ስር እየሰደደ የነበረው ስልጣኔ በዘመኑ የአውሮጳውያን ስልጣኔ መስፋፋት አይነት በተለያየ አገሪቱ ክፍል እንዳይሰራጭ ያቀጨጨው አንድ ትልቅ እንቅፋት እንደነበር በታሪክ አጥኝወች ዘንድ ይጠቀሳል [5]
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.