ሊሻሊሾ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ሊሻሊሾ
Remove ads

ሊሻሊሾ (ሮማይስጥAmaranthus caudatus) ወይም ደግሞ የፈረንጅ ጤፍ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ክረምታዊ አባቢ እጽ ዝርያ ነው። በአሉማ ወገን (Amaranthus) ውስጥ ነው።

More information ?ሊሻሊሾ, ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ ...
Remove ads

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

የህብራበባ ቀይ ቀለም በውስጡ ካሉት ጥንተ ንጥሮች ይወለዳል።

አስተዳደግ

ሊሻሊሾ ከ1 እስከ 3 ሜትር ሊደርስ ይችላል፣ ሙሉ ፀሐይ ይሻለዋል። ልዩ ልዩ ሁናቴዎች እርጥብ ሆነ ደረቅ ይችልበታል። ከዘር በቀላል ይታደጋል። እቤት ውስጥ ይጀመርና ከመጨረሻ ውርጭ በኋላ ከቤት ውጭ መዛወር ይችላል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

አንዴስ ተራሮች ከተገኙት አሉማ ዝርዮች ዋንኛው ሲሆን «ኪዊቻ» ይሉታል። እንደ ብዙ ሌሎች አሉማዎች የዚህ ዝርያ መነሻ ከአሜሪካዊ ግሞጂዎች ነው።

የተክሉ ጥቅም

ከተክሉ ብዙ ክፍሎች ከነቅጠሎቹና ዘሮቹም ሊበሉ ይቻላል፣ በተለይም በሕንድ አገርና በደቡብ አሜሪካ ለምግብነት ይጠቀማል።

በኢትዮጵያ ቅጠሉ ተፈልቶ ይበላል፣ ዘሩም በአጥሚት ወይም በእንጀራ ሊጨመር ይችላል።

ኮንሶ ዘሮቹ ሲበሉ፣ ቻቃ የተባለ መጠትም ለማዘጋጀት ይጠቀማሉ። በደቡብ ኦሞ የአገዳ ቡቃያ በአሪ ብሔር ይበላል። በጉራፈርዳ ጅማ፣ የሊሻሊሾ አረቄ ወይም «ቦርዴ»፣ የሊሻሊሾ ቂጣ፣ እና ለሕፃን የሊሻሊሾ አጥሚት ይሠራሉ።[1]

በኢትዮጵያም የኮሶ ትል ለማስወጣት ተጠቅሞታል። [2]


በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Amaranthus caudatus የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።

References

Loading related searches...

Wikiwand - on

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Remove ads